Song Lyrics

አባት አለኝ

የማይነጋ ለሊት የለም የማይነጋ (x4) ታሪክ ቀያሪ እግዚአብሔር ተአምርን ሰሪ እግዚአብሔር ፀሎትን ሰሚ እግዚአብሔር ሰውን አክባሪ እግዚአብሔር ታሪክ ቀያሪ እግዚአብሔር ተአምርን ሰሪ እግዚአብሔር ሁሉን በጊዜዉ እግዚአብሔር ዉብ አርጎ ሰሪ እግዚአብሔር ያ መልካም እግዚአብሔር ያ ቸሩ እግዚአብሔር ያ ደጉ እግዚአብሔር ያ ታማኝ እግዚአብሔር (x2) የስንፍናን ቃል ሲፈልግ ጠላት ማለዳ መቶ ነፍሴን ሲያውካት እርሱም ሲዳዳ ቃሉን ሰምቼ የማዝን መስሎት ብዬ እስከመቼ እኔ ግን ሰማይ ወደ ላይ ሳይ ነገሬን ትቼ የሱሴን ሳይ ጌታን ሳመልከዉ በእምነት ሳልፈራ የሱስ ነገሬን ዉብ አርጎ ሰራ ያ መልካም እግዚአብሔር ያ ቸሩ እግዚአብሔር ያ ደጉ እግዚአብሔር ያ ታማኝ እግዚአብሔር በፀሎት ቤቴ እርሱን ጠብቄ አፍሬ አላዉቅም ቀርቶ ከቤቴ ልመናዬንም ፈጥኖ ይሰማል የልቤን ሁሉ እርሱ ይረዳል ይህን ጠንቅቄ እኔ አዉቃለዉ የጠራኝ ጌታ የታመነ ነዉ መልካም መልካሙን ያስብልኛል ምንም ሳይሰስት ያደርግልኛል ያ መልካም እግዚአብሔር ያ ቸሩ እግዚአብሔር ያ ደጉ እግዚአብሔር ያ ታማኝ እግዚአብሔር አባት አለኝ ቸር አባት አለኝ አባት አለኝ ደግ አባት አለኝ አባት አለኝ ሁሌ የሚያየኝ (x2) (አባት አለኝ ከቶ ማይጥለኝ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection