ኀጢአት መሆኑን እየተረዳን በደምብ አውቀነው የምንአለበት ተዉ ባክህን ብለን አለፍነው በስግ ስሜት እየተነዳን ስንሸፋፍነው ያወቅነው መስሎን እንዲያው በመላ የዘመኑ ሰው በሰንበት ብቻ ስንንመላለስ ልማድ ሆኖብን አይፈሪሳዊ እያለ ጌታ ግብዞች ሲለን እንደ መቃብር ከላይ ስንታይ ኖራ ተቀብተን ቅሚያና ዝርፊያ ውስጣችን ሞልቷል በመንፈስ ላየን አዝ፦ ይቅርብን እንተው ይቅርብን እንተው ለእኛ ሚሆነው ጌታ ብቻ ነው (2x) ትንኝ አጥርተው ግመል እየዋጡ ቢመላለርሱ የበግ ለምድ ለብሰው ለታይታ ብቻ ጻድቅ ቢመስሉም ጌታ ይመጣል በእጁ መርሽ ይዞ ቤቱን ሊያጠራ ዝም ብሎ አያይም በመቅደሱ ውስጥ ኀጢአት ሲደራ ስንዴና እንክርዳድ ጐተራ አይገባም ብደምብ ሳይጠራ ከመንጋው መሃል ቢመሳሰሉ ሆኖ በጋራ ጌታ ሳይለው ይህ ክርስቲያን ነው ሰው ሁሉ ቢለው መጋፋት አይደል የእርሱ መለኪያው ጌታን መኖር ነው አዝ፦ ይቅርብን እንተው ይቅርብን እንተው ለእኛ ሚሆነው ጌታ ብቻ ነው (2x) ምንም ቢማሩ ለውጥ ከሌለ መምህር ቢባሉ አያስደንቅም ወረቀት ይዘው ዲግሪ ቢጭኑ አንቱ ቢባሉ ለምን ይጠቅማል ሕይወት ከሌለው ዝናና ክብር በምድር ያለው ሁሉም ጠፊ ነው እንዲያው በጭፍር ምንም ሳይገባው የጌታ አላማው ቢሰብክ ቢዘምር ቃሉን አጣፍጦ ወደድኩህ ቢለው ለራሱ ክብር እያመቻቸ የኖረውን ሰው ተጠቀመብኝ አለ እንጂ እራሱ ጌታ መች አለ አዝ፦ ይቅርብን እንተው ይቅርብን እንተው ለእኛ ሚሆነው ጌታ ብቻ ነው (2x)