በአፍላ ልጅነት እራዕይ ሰጥቶኝ ውስጤ እይፈላ እንዴት ያስችለኝ በዚህ ደስ ብሎኝ ብሰብክ ባወራ መንገድ ዘጋብኝ ያባላጋራ በአጭር ቀጨሁት ብሎ ሲዝናና ጥሼው መሄዴን አላየምና ተጥዬ የምቀር መስሎታልና እንዲህ የዋዛ መቼ ሆንኩና መስሎት የፈራሁ ገና ለገና ጉዱ ፈላበት ነካካኝና አዝ፦ ወረደ አምላኬ ከሃያላን ጋራ ከሰማይ መቅደሱ አያበራ ወረደ አምላኬ ከሃያላኑ ጋር በሰልፉ ስለ እኔ ሊዋጋ አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ አልመለስም ቅባቱን ይዤ አልመለሰም አምላኬን ይዤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ አልመለስም ቅባቱን ይዤ ምንም ቢያወራ እኔ ላልፈራ አታመልጠኝም ቢል ለፉከራ ዛቻ ፉከራ ላይሆን ላይሰራ ጸጉሬን ዐይነካም ምን ቢንጠራራ ዝምበል ጠላቴ እስኪ አትፎክር ከአንተ የሚበልጥ አለኝ እግዚአብሔር ሰልፉ የእግዚአብሔር መሆኑን ሳያውቅ ዘሎ ገባበት አቤት መናናቅ ወይ አለማሰብ አዬ መሳሳት መቼ ይሆናል በእሳት መጫወት አዝ፦ ወረደ አምላኬ ከሃያላን ጋራ ከሰማይ መቅደሱ አያበራ ወረደ አምላኬ ከሃያላኑ ጋር በሰልፉ ስለ እኔ ሊዋጋ አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ አልመለስም ቅባቱን ይዤ አልመለሰም አምላኬን ይዤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ አልመለስም ቅባቱን ይዤ ጠላቴ ሲያየኝ መስሎት ማልበቃ ጌታ ግን ቀባኝ አድርጐ አለቃ ሰው ሁሉ ሲያየኝ አንተ ብላቴና አትችለውም ህጻን ነህና ህጻን ብመስልም ምንም ማልረባ ገልብጬው መጣሁ ያንን ገለባ ሲያስብ ጠላቴ በአምላኬ ማፍር እኔ ሳለቅስ እርሱ ሊፎክር ተአምር ሰራና የእኔ እግዚአብሔር ከዐይኔ አስወገደው እስኪ ልዘምር አዝ፦ ወረደ አምላኬ ከሃያላን ጋራ ከሰማይ መቅደሱ አያበራ ወረደ አምላኬ ከሃያላኑ ጋር በሰልፉ ስለ እኔ ሊዋጋ አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ አልመለስም ቅባቱን ይዤ አልመለሰም አምላኬን ይዤ አልመለስም ቅባቱን ይዤ አልመለስም ሰልፉን ፈርቼ አልመለስም ቅባቱን ይዤ