አዝ፦ በንሰሃ ለመመለስ ወደ ዙፋንህ ለመድረስ መጥተናል ተቀበለን በደላችንን ይቅር በለን (2x) የቤትህን ተድላን ሰላም ተቀምተን ከፍ ካድረከን ከጉያህ ውስጥ ወተን ጠላትህ ረጋግጦ ብዙ አጐሳቁሎናል በምህረትህ ጐብኘን ፊትህ ይሻለናል የዓለምን ምርኩዝ ኀጢአት ተደግፈን በስራ ሳንለይ እንዲሁን በአፋችን አሁን ምኑ ላይ ነው የእኛ ሕይወታችን በጌታ ቤት ሆነን እየተገፋፋን አዝ፦ በንሰሃ ለመመለስ ወደ ዙፋንህ ለመድረስ መጥተናል ተቀበለን በደላችንን ይቅር በለን (2x) ይብቃን አሁን ይብቃን እንደሬት ይምረረን ኀጢአትን እንጥላው በንሰሃ ታጥበን እንደጌታ ያለ የትም አናገኝም አይተነው የለም ወይ ቆሻሻውን ዓለም በስም ክርስትና ብለን ተሸፍነን በቃላት ታጅበን ለሚያየን ሰው መስለን ምንም አልተለወጥን ገባ ብሎ ለአየን ሌላ ስም የለንም ይህ ነው ታሪካችን አዝ፦ በንሰሃ ለመመለስ ወደ ዙፋንህ ለመድረስ መጥተናል ተቀበለን በደላችንን ይቅር በለን (2x) እንደ ምህረትህ ብዛት እንደቸርነትህ መጠን ለአምጻችንና ለኀጢአታችን ፍሬ አሳልፈህ አትስጠን ዘር ቀለምን ለየን የእኛ ጉድ አያልቅም አንድ ያደረከንን ጌታ ለዘለዓለም ዐይናችን ጨልሞ ከፋፍለን ብናይም ባሪያ ጨዋ ብሎ ቃሉ አይለያየንም ክርስቶሥን ለብሶ አይሁድ ግሪክ የለም የጸና ቃል አለን ማንም አይሽረውም እንመለስ አሁን ጌታ መሃሪ ነው እርሱ ይቅር ሊለን ሁሌም ዝግጁ ነው አዝ፦ በንሰሃ ለመመለስ ወደ ዙፋንህ ለመድረስ መጥተናል ተቀበለን በደላችንን ይቅር በለን (2x) አጣፍጠን ብንዘምር አንደበትን ስለን ጌታ ሚፈልገው መቀደሳችንን ድምጹን እናዳምጠው እስኪ እንተላለፍ በስራ እንለይ በቃል ከመለፍለፍ የድፍረት ኀጢአት አናፍርም ስንሰራ እንደ ኤሊ ልጆች በነውር ስንኮራ ምክር ግሳጼንም እንሰማም ብለናል በመስዋዕቱ ሥጋ ልባችን ደንድኗል አዝ፦ በንሰሃ ለመመለስ ወደ ዙፋንህ ለመድረስ መጥተናል ተቀበለን በደላችንን ይቅር በለን (2x)