ራሱን ጽድቅ ላቆመ ደህና ነኝ ለሚለው ሰው፣ ጸጋው ምኑ ነው? ምህረቱስ መች ገብቶት ሊያደንቀው፤ ልምምዱ ላስመሰካው ሥርዐት መፈጸሙ፣ ጸጋው ምኑ ነው? ኃጢአቱስ መች ገብቶት ሊጠላው። ስላልተገኘ አንድም የሚበቃ፣ ስላልተገኘ- አንድም የሚያሟላ፤ ስላልተገኘ- አንድም እርሱው መጣ፣ በራሱ ክንድ ድህነትን አመጣ። የዓለም ኀጢአተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊድናችሁ፤ የዓለም ኀጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ብለው ብለው ልችለው ሕጉን ልተገብረው፣ ታገልሁ ልሠራ- የሱን ጽድቅ መስፈርት ልደርሰው፤ ብለው ብለው ልሆነው- ሰው መሆንን እንዳለው፣ ተገኘሁ እዛው- ከክብሩ ጎድዬ ሙት ሆኜ። ስለማትችይው እኔ ሆንኩት አለኝ፣ እመሃል ገብቶ ከራሱ አስታረቀኝ፤ ስለማትችይው እኔ ልክፈል አለኝ፣ ይቅርታን ሰጥቶ በፀጋው ቀረበኝ የዓለም ኀጢአተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊድናችሁ፤ የዓለም ኀጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ወረደ- ታረደ፣ የእኔን እዳ ወሰደ፤ ወረደ- ማለደ፣ በደሌን አ-ስወገደ። የጽድቄን ጥግ አሳየኝ የኔ አለመብቃቱን፣ እጅግ ማደፉን ፤ ግን ሰጠኝ ፍጹሙን የራሱን። ስለሚራራ ስላልጨከነብኝ፣ የሕይወትን መንገድ ራሱን አሳየኝ፤ ስሚራራ- ስለሚወድ ማዳን፣ ዕዳዬን ከፍሎ ነፃነት አወጣኝ። የዓለም ኀጢአተኞች እንኳን ደስ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ መጥቷል ሊድናችሁ፤ የዓለም ኀጢአተኞች እንደኔ ያላችሁ፣ ኢየሱስ ያድናል በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ኢየሱስ ሠርቶል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ፣ አየሱስ ሆኖታል- በእርሱ ተስፋ አላችሁ። ኢየሱስ ችሎታል በእርሱ ተስፋ አላችሁ።