ና ጌታ ሆይ፣ ወደነገሬ- ወደ ችግሬ፤ ና ጌታ ሆይ፣ ወደ ፍርሃቴ ወደ ስጋቴ … እህህ ሊረዳኝ የሚችል የምታመንበት፣ የለኝም አንድም ሰው ማዳን የሚውቅበት፤ አንተን ነው የማውቀው ስታድን በታምር፣ ምህረትህ ያውጣኝ ከከበበኝ ሽብር። ና ጌታ ሆይ፣ ወደነገሬ- ወደ ችግሬ፤ ና ጌታ ሆይ፣ ወደ ፍርሃቴ ወደ ስጋቴ … እህህ ማዕበልና ሞገድ አለፉ በላዬ፣ ብዘንፍ ከፍቃድህ ወደ እኔ ኮብልዬ፤ እንዳዘዝከኝ ሳይሆን ሄጄ እንደ ምኞቴ፣ ስብራትን ጋበዝሁ ጠራሁ ወደ ሕይወቴ። ና ጌታ ሆይ፣ ወደነገሬ- ወደ ችግሬ፤ ና ጌታ ሆይ፣ ወደ ፍርሃቴ ወደ ስጋቴ … እህህ ዉጦ እንዲያስቀረኝ ከዛተብኝ ስምጠት፣ አውጣኝ ከዚህ ባህር ከተቀበርሁበት። ተስፋዬ አንተ ነህ እጠብቅሃለሁ። ተስፋዬ አንተ ነህ እጠብቅሃለሁ። ና ጌታ ሆይ ና ረዳቴ ና ፈርቻለሁና፣ ና ጌታ ሆይ ና ረዳቴ ና ብቻዬን ነኝና ፤ ና