Song Lyrics

እጄን ይዘህ ምራኝ

Zeritu Kebede
Matsinanatih
ዉዴ ኢየሱስ የኔ ደስታ የምወድህ ጌታዬ፤ ያይኔ ትኩረት ባንተ ላይ ነው፣ መልካሙ እረኛዬ። ጌታ ኢየሱስ የኔ ጉዳይ፣ የመኖር ዓላማዬ፤ የኔ ምለው የማዝበት፣ ኑሮ ካበቃ ቆየ። ለነፍሴ ሆንክላት ፍቅሯና ሕይወቷ፣ ለህመሟ ሁሉ ፍቱን መድሃኒቷ፤ መሄጃ የለኝም ወዴት እሄዳለሁ፣ የሕይወት ቃል ካለህ ካንተ ደርሻለሁ። ለመኖር እንድችል እንዳወራኝ ቃልህ፣ በራሴ አይሆንም ታሰፈልገኛለህ፤ ተማሪህ ነኝና ያንተ ደቀመዝሙር ፣ ምራኝ የኔ ጌታ የኔ ደግ መምህር። እጄን ይዘህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ ፣ እጄን ይዘህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ፤ ድምጽ ልከህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ፣ ድምጽ ልከህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ፤ እንዳልከስር እንዳልባዝን፣ እንዳልዘገይ- እንዳልባክን። እንዳልከስር እንዳልባዝን፣ እንዳልዘገይ- እንዳልባክን። የእግዚአብሔር ምስጢር ለኔ ተገልጠሃል፣ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳውቅህ ወደሃል፤ ማህተም አለብኝ የተገዛሁበት ፣ በፈሰሰው ደምህ በ- በመስቀሉ መስዋዕት። መኖር አልፈልግም ዓለምን መስዬ፣ አካሄዴን አቅናው አርቀኝ ጌታዬ፤ እንዳገለግልህ እንደ አሳብህ ፈቃድ፣ እርዳኝ የኔ ጌታ ሕይወቴን አስለምድ። እጄን ይዘህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ ፣ እጄን ይዘህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ፤ ቃልህን ገልጠህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ፣ ቃልህን ልከህ ምራኝ ጌታ ኢየሱስ፤ እንዳልከስር እንዳልባዝን፣ እንዳልዘገይ- እንዳልባክን። እንዳልከስር እንዳልባዝን፣ እንዳልዘገይ- እንዳልባክን። መንፈስ ቅዱስ የኔ ረዳት፣ ትሁቱ ጓደኛዬ፤ ልበድልህ አልፈልግም፣ በከንቱ ረብ ታልዬ። መንፈስ ቅዱስ -የኔ ብርታት፣ ከባዱን መቻያዬ፤ በእኔ ሳይሆን ባንተ ምሪት፣ ለመኖር ነው ምርጫዬ። ያላንተ አይሆንም ያላንተ አልችልም፣ አንዱንም ጥቂቱንም። ያላንተ አይሆንም ያላንተ አልችልም፣ አንዱንም ጥቂቱንም። ጌታ ኢየሱስ የኔ ሰላም፣ ጽድቄ ቅድስናዬ፤ ያረፍኩብሀ ደህንነቴ፣ ለዘላለም ተስፋዬ።
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection