የተገኘሁበት የዳንሁበት ታምር ይበቃኝ ነበረ አመስግኜ እንድኖር፤ ያስጀመርከኝ መንገድ ለኔ የበራልኝ፤ አለ እየጨመረ እያበዛህልኝ፣ አለ እየጨመረ እያበዛህልኝ፤ አለ እየጨመረ እያበዛህልኝ፣ አለ እየጨመረ እያበዛህልኝ። በዛ ብርሃንህ በዛ፣ ሕይወትህ በዛ፣ ለኔ ጸጋህ በዛ፤ በዛ ምህረትህ በዛ፣ ሰላምህ በዛ፣ ቸርነትህ በዛ፤ አስገረምከኝ ዛሬም እንደገና … አስገረምከኝ ዛሬም እንደገና… አስተማርከኝ ዛሬም እንደገና … አስተማርከኝ ዛሬም እንደገና … ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና። በዛ ይቅርታህ በዛ፣ ትዕግሥትህ በዛ፤ ለኔ ፍቅርህ በዛ። አስመለጥከኝ ዛሬም እንደገና፣ አስመለጥከኝ ዛሬም እንደገና፤ ደረስክልኝ ዛሬም እንደገና፣ ደረስክልኝ ዛሬም እንደገና። ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና። አንተ ቃልኪዳን አክባሪ፣ ታማኝ ነህ ለሕዝብህ ጌታዬ፤ አንተ የማትጥል ወዳጅ ፣ መልካም ነህ ቀን በቀን ጌታዬ፤ አንተ በጎ ነገር ሁሉ፣ የሚመነጭብህ ጌታዬ፣ አንተ መማር የማይደክምህ፣ ታጋሽ ነው መውደድህ ጌታዬ። አንተ ሊፈስ ያለን ዕንባ፣ ቀድመህ የምታብስ ጌታዬ፤ አንተ የዛለውን ጉልበት፣ ኃይልን የምታድስ ጌታዬ። አንተ መረን የማትለቅ፣ ፍቅርህ የሚገስጽ ጌታዬ፣ አንተ መልክህን በኔ ላይ፣ በእጆችህ የምቴ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና፣ ልስጥህ ምስጋና። አንተ ቃልኪዳን አክባሪ፣ ታማኝ ነህ ለሕዝብህ ጌታዬ፤ አንተ የማትጥል ወዳጅ ፣ መልካም ነህ ቀን በቀን ጌታዬ፤ አንተ በጎ ነገር ሁሉ፣ የሚመነጭብህ ጌታዬ፣ አንተ መማር የማይደክምህ፣ ታጋሽ ነው መውደድህ ጌታዬ። አንተ ጌታዬ አንተ ጌታዬ አንተ ጌታዬ አንተ ጌታዬ