Song Lyrics

ትናንትና ዛሬ

Zeritu Kebede
Matsinanatih
ትናንት ይህን ጊዜ ትናንት ይህን ሰዓት፣ ትናንት ባለማወቅ ትናንት በጥፋት፤ ትናንት በዚህ ጊዜ ትናንት በዚህ ሰዓት፤ ትናንት በጨለማ ትናንት በክፋት። ነበረ ሕይወቴ ከብርሃኑ ማዶ፣ ጌታ እስኪታደገኝ ሊያስመልጠኝ ወዶ፤ ትናንት ሽብር ነበር አለመረጋጋት፣ ለነፍሴ ማረፊያ ከለላ በማጣት። ግን አለፈ ትናንት ላልመለስበት፣ አየሱስ አገኘኝ በማይጥለው ምህረት፤ ዛሬ እኔ ደህና እረፍት ያገኘሁ ሰው፣ እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያደረገው። ትናንት ይህን ጊዜ ትናንት ይህን ሰዓት፣ ትናንት በጥርጥር ትናንት በፍርሃት፤ ከሙታን መካከል ነበረ ምድቤ፣ የዉሸት አባት ልጅ ጠላት በአሳቤ፤ የሥጋዬን ፈቃድ ምኞቴን ተከታይ፣ ኃጢአት የገዛኝ ሞት የሚያስፈራራኝ። ግን አለፈ ትናንት ላልመለስበት፣ ኢየሱስ አገኘኝ በማይጥለው ምህረት፤ ዛሬ እኔ ደህና እረፍት ያገኘሁ ሰው፣ እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያደረገው። ስለተገዛሁኝ ለእርሱ ሳልወደው ለወደደኝ፣ በዓለም የማይገኘውን ሰላሙን አወረሰኝ፤ ስለተገዛሁኝ ለእርሱ በፍቅሩ ለጣመነደኝ፣ አሮጌው ነገር አለፈ አዲስ ሰው አደረገኝ። ድንቅ ልዩነት በኢየሱስ አየሁ፣ ጨለማው አልፎ ብርሃን ሆኛለሁ፤ ድንቅ ልዩነት ሆነልኝ በእርሱ፣ ስላመንኩበት ረድቶኝ መንፈሱ። በቃ አለፈ ትናንት ላልመለስበት፣ አየሱስ አገኘኝ በማይጥለው ምህረት፤ ዛሬ እኔ ደህና እረፍት ያገኘሁ ሰው፣ እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያደረገው። እግዚአብሔር ይመስገን ይህን ያደረገው(3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection