አዝ፦ እውነት ተገልጦልኛልና ወደኋላ አልመለስም (2x) በአለማወቅ የኖርኩባቸው ዘመናቶቼ ዳግመኛ እንዳላያቸው በአምላኬ እረሳኋቸው (2x) ጸያፍ ነበረ ምግባሬ በደሌም በዝቶ ነውሬ እርሱ ባይረዳኝ ረድኤቴ አክትሞ ነበር ሕይወቴ ከገደል አፋፍ መለሰኝ የሞትን ጽዋ ሳልቀምሰው እራርቶልኛል በፍቅሩ ምሥጋና ክብር ይድረሰው ለአምላኬና ለሥሙ ክብር ስዘምር ውዬ ስዘምር ባድር ለአምላኬማ አይገልጽልኝም የውስጥ የልቤን ያለኝን ፍቅር (2x) አዝ፦ እውነት ተገልጦልኛልና ወደኋላ አልመለስም (2x) በአለማወቅ የኖርኩባቸው ዘመናቶቼ ዳግመኛ እንዳላያቸው በአምላኬ እረሳኋቸው (2x) የጽድቅን መንገድ ስልሳውቀው ጉዙው አድክሞኝ ዝያለሁ እረፍት የሌለው እርካታ ውሸት ነው የዓለም ደስታ መውጣት መውረዱ መልፋቱ እርባን አቢስ ነው ሁሉ ከንቱ ዓይኖቹ በርተው ላየው ሰው የኢየሱስ መሆን መታደል ነው ለአምላኬና ለሥሙ ክብር ስዘምር ውዬ ስዘምር ባድር ለአምላኬማ አይገልጽልኝም የውስጥ የልቤን ያለኝን ፍቅር (2x)