ምን እላለሁ እኔ ምን እላለሁኝ ምን እላለሁኝ መነ እላለሁኝ ስትረዳኝ እያየሁ ስታግዘኝ ስታግዘኝ ስታግዘኝ የቱን ዘምሬ የቱን እተዋለሁ ለኔ ያረክልኝ ከአይምሮ በላይ ነው ለኔ ያረክልኝ ከአይምሮ በላይ ነው መልካም ነህ ቢሉህ መልካምነትስ መቼ ይገልጽሃል ፍቅር ነህ ቢሉህ የፍቅር ልኩ መቼ ይገልጽሃል ኧረ ማን ልበልህ ማን ልበልህ ፡ ቃል አጣሁልህ ከተጣልኩበት አዘቅት መጥተህ ከጠላቴ እጅ እኔን ተናጥቀህ በደምህ ገዝተህ የአንተ ካረከኝ እነዴት አልዘምር እንዴት አልቀኝ ዛሬማ በላይ ሆኖአል ስፍራዬ ፡ በአብ ቀኝ ሆኖአል መቀመጫዬ ክብር ምሥጋና ለአንተ ይድረስህ እድሜ ዘመኔን ልዘምርልህ እንዴት ላመስግንህ ኧረ እንዴት ላወድስህ ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ ሁለንተናዬን ለአንተ ሰጥቼ በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ ይኽው ላመልክህ መጥቻለሁ መልካም ነህ ቢሉህ መልካምነትስ መቼ ይገልጽሃል ፍቅር ነህ ቢሉህ የፍቅር ልኩ መቼ ይገልጽሃል ኧረ ማን ልበልህ ማን ልበልህ ቃል አጣሁልህ ሙት የነበርኩኝ በበደል ብዛት ሕያው አረከኝ ነፍሴን ቀደስካት ከክርስቶስ ጋር ሕይወት ሰጠኽኝ በትልቅ ፍቅርህ እንዲያው ወደድከኝ ጽድቄ ነህና ቅድስናዬ ፡ እንከን የሌለህ ንጽህናዬ ፡ ብቃት የለኝም የምለው የእኔ ቤዛ ባትሆነኝ አንተ መድኅኔ እንዴት ላመስግንህ ኧረ እንዴት ላወድስህ ከቃላት በላይ ነፍሴን አፍስሼ ሁለንተናዬን ለአንተ ሰጥቼ በፍቅርህ ጉልበት ተረትቻለሁ ይኽው ላመልክህ መጥቻለሁ አመልክሃልሁ ዘላለሜ ኢየሱሴ የእንተ ነው አመልክሃለው የእኔ ጌታ ዘመኔን ውረሰው ዘመኔ የአንተ ነው ኑሮዬ የአንተ ነው