Song Lyrics

ምሥጋና

Tewodros Tadesse
Yekasa Zemen
ፈረሱንና ፈረሰኛውን በባሕር የጣለ እኛን አሻግሮን በሚያስፈራ ግርማው ከፊት እየመራ ነጥቆ ያስመለጠን ከዚያ ባለጋራ (2x) አዝ፦ ትላንት የረዳን ያገዘን ጌታ ዛሬም በዙፋኑ አለና እንጨምር ምሥጋና (2x) ብዙ ብዙ (ምሥጋና) ከልባችን (ምሥጋና) እንሰዋ (ምሥጋና) ለጌታችን (ምሥጋና) (2x) ሌሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና እስራኤልን የሚጠብቅ ለአፍታ ደክሞ አያውቅም መንገድ አስጀምሮ ጥሎ የማይጠፋ የማይሻር ኪዳን አለው ጽኑ ፍቅር ቀን ቢከፋ እንደኃያልና እንደጨካኝ ወጥቶ በሰልፉ ሜዳ ላይ ውጊያውን ተዋግቶ ድል አድርጐ ባለድል ያደረገን እርሱ ነው ይክበር ይንገሥልን ወደን እናምልከው ፈቅደን እናምልከው አዝ፦ ትላንት የረዳን ያገዘን ጌታ ዛሬም በዙፋኑ አለና እንጨምር ምሥጋና (2x) ብዙ ብዙ (ምሥጋና) ከልባችን (ምሥጋና) እንሰዋ (ምሥጋና) ለጌታችን (ምሥጋና) (2x) ሌሊት በእሳት አምድ ቀኑን በደመና እስራኤልን የሚጠብቅ ለአፍታ ደክሞ አያውቅም መንገድ አስጀምሮ ጥሎ የማይጠፋ የማይሻር ኪዳን አለው ጽኑ ፍቅር ቀን ቢከፋ ብዙ ብዙ (ምሥጋና) ከልባችን (ምሥጋና) እንሰዋ (ምሥጋና) ለጌታችን (ምሥጋና) (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection