Song Lyrics

ድኛለሁ

Tewodros Tadesse
Yekasa Zemen
አንዴ ድኛለሁ ጽድቅን ጸድቄ በከበረው ደም ከአብ ታርቄ የቃልኪዳን ልጁ አድርጐኛል ከእርሱ ፍቅር ማን ይለየኛል (2x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ በአንዱ አዳም ምክንያት ሞት ወደእኛ መጣ አልታዘዝ ብሎ ከገነት ሊወጣ አምላክ ሥጋ ለብሶ ወደምድር ወረደ ራሱን ቤዛ አድርጐ ሊያጸድቀን ወደደ አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ እግዚአብሔር ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ ሎሌ ሳልሆን ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ ዘምሬ አልጠግብም ስለመዳኔ ሌላው ሌላውማ ትርፍ ነው ለእኔ (2x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ አንዴ ድኛለሁ ጽድቅን ጸድቄ በከበረው ደም ከአብ ታርቄ የቃልኪዳን ልጁ አድርጐኛል ከእርሱ ፍቅር ማን ይለየኛል (2x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ በማመኔ ብቻ ሳልደክም ሳልለፋ ዘለዓለሜ አማረልኝ አምላክ ክብሩ ይስፋ እውነትም መንገድም ሕይወትም እርሱ ነው ኢየሱስ ያድናል ብዬ እመሰክራለሁ አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ እግዚአብሔር ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ አቤት አቤት እገረማለሁ እደነቃለሁ ሎሌ ሳልሆን ልጅ በመሆኔ እደሰታለሁ ዘምሬ አልጠግብም ስለመዳኔ ሌላው ሌላውማ ትርፍ ነው ለእኔ (2x) አዝ፦ (ድኛለሁ) ስሜ በሕይወት (ድኛለሁ) መዝገብ ተጽፎ (ድኛለሁ) አዲስ ሆኛለሁ አሮጌው አልፎ (ድኛለሁ) ስፍራ እንደሌለው (ድኛለሁ) ልቤ እንዳይሰጋ (ድኛለሁ) ብሎ ነህ አለኝ የስሜ ዜጋ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection