Song Lyrics

በድካሜ

Tewodros Tadesse
Yekasa Zemen
አዝ፦ ኃይልህ በድካሜ ተገልጦ ስትሰራ አይቻለሁ ከእኔ ምለው የለም የሆነው ይህ ሁሉ በአንተ ነው ላከብርህ ዘንድ ይገባኛል ቸሩ አባቴ ፊትህ ወድቄ ተንበርክኬ በጉልበቴ ዝቅ ብዬ ላክብርህ ታይብኝ ከፍ ብለህ (2x) እንደልጅ አይተኸኝ በልጅነት ወራት ክፉ አመሌን ቻልከው የምህረትህ ብዛት አልጨከንክብኝም እንድሰጥ ታልፌ ስንቶችን ከመንገድ ካስቀረው ተርፌ አለሁ በገናዬን ዛሬም አልሰቀልኩም ስለቸርነትህ/ስለደግነትህ መዘመር አልተውኩን (2x) አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ጌታ ውለታህ ብዙ ነውና አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ኢየሱስ ውለታህ ብዙ ነውና (2x) አዝ፦ ኃይልህ በድካሜ ተገልጦ ስትሰራ አይቻለሁ ከእኔ ምለው የለም የሆነው ይህ ሁሉ በአንተ ነው ላከብርህ ዘንድ ይገባኛል ቸሩ አባቴ ፊትህ ወድቄ ተንበርክኬ በጉልበቴ ዝቅ ብዬ ላክብርህ ታይብኝ ከፍ ብለህ (2x) በውድቀቴ ስቀህ ጀርባ አልሰጠኸኝም ዓይንህም እንዳየች አልበየንክብኝም ይልቅ አስጠጋኸኝ መከርከኝ ለልቤ ከቶ እንደማይበጅ ሰውኛው ሃሳቤ ለተፍገመገመው ኃይልን የሰጠኸው የሳተውን ደግሞ ቀርበህ የመለስከው የእንደገና አምላክ አደረከኝ ቀና ሃፍረቴን ሸፍነህ የቤቴን ገበና አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ጌታ ውለታህ ብዙ ነውና አያምርብኝም በእኔ ስንፍና ኢየሱስ ውለታህ ብዙ ነውና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection