አዝ፦ ያኖራል የታመንኩት አምላክ ያኖራል ተዐምር/ድንቅን እየሰራ ያኖራል ተጸጽቼ አላውቅም ያኖራል ሆኜ ከእርሱ ጋራ (2x) በበረሃው ላይ ምድረ በዳው ላይ ምንጭን አፍልቆልኝ ጠጥቻለሁ ከአስጨናቂው ጥሜ ረክቻለው (2x) መከራው በዝቶ እንዴት ይኖራል እያሉ ሲያወሩ እኔ ግን አለሁ እየዘመርኩኝ በዝቶልኝ ተዐምሩ (2x) ለታመነበት ጌታ ነው ለተደገፈው ፍፁም አይጥልም አይረሳም ተስፋ ላደረገው (2x) አዝ፦ ያኖራል የታመንኩት አምላክ ያኖራል ተዐምር/ድንቅን እየሰራ ያኖራል ተጸጽቼ አላውቅም ያኖራል ሆኜ ከእርሱ ጋራ (2x) በበረሃው ላይ ምድረ በዳው ላይ ምንጭን አፍልቆልኝ ጠጥቻለሁ ከአስጨናቂው ጥሜ ረክቻለው (2x) ልዑል መጠጊያ ጥላ የሆነው ሁሉን በእርሱ ጥሎ ጻድቅ ሳይፈራ ልክ እንዳንበሳ ያድራል (2x) ሥሙ የጸና ግንብ ነው ዘመን የማይሽረው ኢየሱስ ብሎ ያመልጣል ክፉ ሳይነካው (2x)