Song Lyrics

ለውጠኝ

Tewodros Tadesse
Yekasa Zemen
ማደግ እሻለሁ አንተን መምሰል ግን አቅቶኛል ክብሬን መጣል የዚህ ዓለም ነገር ልቤን አድክሞት ለአንተ እንዴት ልኖር ለሌላው ሳልሞት የዚህ ዓለም ነገር ልቤን አዝሎት ለአንተ እንዴት ልኖር ለሌላው ሳልሞት አዝ፦ ለውጠኝ (3x) ለውጠኝ (3x) ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ ደካማ ሰው እኔ ነኝ እንዲያው አያለሁ ልብ ብዬ እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ (2x) እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ ወደራስህ ሳበኝ (2x) ከካቻምና የአምና ከአምናው የዘንድሮ ሕይወቴ ካልታየ ስምህ በእኔ ከብሮ መኖርስ ምንድንነው ዘመን ማስቆጠሩ እንዲያው መመላለስ ፍሬን ሳያፈሩ አዝ፦ ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ ደካማ ሰው እኔ ነኝ እንዲያው አያለሁ ልብ ብዬ እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ (2x) እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ ወደራስህ ሳበኝ (2x) የእምነት አባቶቼ አንተን አስከብረው የክብርን ሞት አዩ በእምነታቸው ጸንተው ፀጋህን አልብሰኝ አልኑር ተሸንፌ ከሚጠፋው ዓለም ጸጸትን አትርፌ አዝ፦ ቃል ኪዳኔን ያጠፍኩኝ ደካማ ሰው እኔ ነኝ እንዲያው አያለሁ ልብ ብዬ እጮሃለሁ እንዲህ ብዬ (2x) እጄን ያዘኝና አስጠጋኝ ወደራስህ ሳበኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection