አዝ፦ የሰው ምኞቱ ብዙ ነው ሌት ተቀን በልቡ ሚያስበው ዓይን ከማየት አይጠግብም ጆሮም ከመስማት አይሞላም እኔ ግን ክብርህን ማየት ነው ጥማቴ ክብርህን ማየት ነው ጉጉቴ በዚች ምድር ሳለች ሕይወቴ (2x) ከአንተ ሚያገኘውን ፈልጐ የመጣ ከእጅህ ተቀብሎ ዳግመኛ ላይመጣ እንደልቡ መሻት ሁሉን ብትሰጠው አንተ ከሌለኸው ምንኛ ምስኪን ነው (2x) ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል የዚህ ምድር ክብር መች ከልኩስ ያልፋል ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል አዝ፦ የሰው ምኞቱ ብዙ ነው ሌት ተቀን በልቡ ሚያስበው ዓይን ከማየት አይጠግብም ጆሮም ከመስማት አይሞላም እኔ ግን ክብርህን ማየት ነው ጥማቴ ክብርህን ማየት ነው ጉጉቴ በዚች ምድር ሳለች ሕይወቴ (2x) እንደሰው ወግ ልማድ ዓመታት ቆጥሬ ማለፍ አልፈልግም ተራ ኑሮ ኖሬ የተጠራሁለት የክብር ጥሪ ነው ማቅለል አልፈልግም እንደዋዛ ላየው እንደቀልድ ላየው ሰው ዓለሙን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢያጐድል ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል የዚህ ምድር ክብር መች ከልኩስ ያልፋል ምን ይረባዋል ምን ይጠቅመዋል ለፍቶ ያከማቸው ጐተራው ሲሞላ የማይቆርጠው ጥሙ ደግሞ ሲለው ሌላ ሲባክን ይኖራል ርጋታን ፍለጋ ከእረፍት ውኃ ምንጭ ቀርቦ ሳይጠጋ