Song Lyrics

ሳስበው

Tewodros Tadesse
Yekasa Zemen
አዝ፦ ሳስበው (3x) የአምላኬን ምህረት ቸርነቱን ዘምር ያሰኘኛል እንደገና በዋዛ ሚታለፍ መች ሆነና (2x) አላየውም እኔስ እንደዘበት የማይገባኝን ክብር አይቻለሁ ደግሜ ደግሜ ቸር ነህ ብለው ፍቅር ነህ ብለው ደግ ነህ ብለው ቃላት አጥቼ እንጂ ይሄ ሁሉ ሲያንስ ነው (4x) ሞገስ ያገኘሁት አንተን አግኝቼ ነው ኢየሱሴ የሰላሜ ምክንያት መሆንህን ታውቀዋለች ነፍሴ (4x) ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (2x) ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (2x) አዝ፦ ሳስበው (3x) የአምላኬን ምህረት ቸርነቱን ዘምር ያሰኘኛል እንደገና በዋዛ ሚታለፍ መች ሆነና አላየውም እኔስ እንደዘበት የማይገባኝን ክብር አይቻለሁ ደግሜ ደግሜ ክብሬ ነህ ብለው ሞገሴ ብለው ማዕረጌ ብለው ቃላት አጥቼ እንጂ ይሄ ሁሉ ሲያንስ ነው (4x) ልቀኝልህ ቅኔ ብትወደኝ አይደል ወይ ሰው መሆኔ ሰው ሁሉ ሲረሳኝ ያሰብከኝን አልረሳውም እኔ አይተህ እንዳላየስ መች አለፍከኝ አልረሳውም እኔ ከመንገድ ወድቄ ራራህልኝ አልረሳሁም እኔ ቁስሌን ሳትጸየፍ ያከምክልኝ አልረሳውም እኔ ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (2x) ኦ እኔ ማነኝ ኦ ማን ነበርኩኝ ታማኝ አርገህ ቆጥረኸኝ በቤትህ የሾምከኝ እራሴን አውቀዋለሁ ታናሹን ሰው እንተው ነህ ያሰብከኝ/የወሰድከኝ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection