Song Lyrics

የካሳ ዘመን

Tewodros Tadesse
Yekasa Zemen
ሰማይ ምድር ይስማኝ ፍጥረት ያድምጠኝ እግዚአብሔር ያሰበው ጸሎቱ የተሰማ ያ ሰው እኔ ነኝ እኔ ነኝ በቆዘምኩበት ዘመን ፈንታ ከፍ ሊያደርገኝ ደጉ ጌታ መከራዬንም ሊያስረሳኝ ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ ባለቀስኩበት ዘመን ፈንታ ደግሞ ሊያስቀኝ ደጉ ጌታ መከራዬንም ሊያስረሳኝ ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ የካሳ ዘመን አለ ከፊቴ (2x) ልውጣ ልውረሰው ወግድ ጠላቴ ዞርበል ጠላቴ የበቀል ቅባት ስላረፈብኝ ኪዳንህ ፈርሷል ዳግም ላትገዛኝ (2x) ወራሽ ሆኜ ሳለሁ እርስት እንደሌለው የሃዘን የለቅሶ ቤቴን ልታደርገው ወገን ዘመን ያጣ ባይተዋር ብቸኛ ብለህ ስትጣራ ጌታ መጣልኛ በሰው አቆጣጠር ቢመስል የዘገየ እውነተኛ ዳኛ መገፋቴን አየ ጠላቴ ሆይ ስማ ብወድቅ እነሳለሁ በጨለማ ብሄድ ጌታ ብርሃኔ ነው የጠራኝ እግዚአብሔር አይጥልም አውቃለሁ እንዳልሰማ የአንተን ስብከት ውሸታም ነህ የውሸት አባት ፈጣሪዬን ለእኔ ልታማ ብዙ ሞከርክ መች ልታቅማማ እኔስ የማውቀው ይሄን ነው እግዚአብሔር ለእኔ መልካም ነው (እግዚአብሔር ለእኔ መልካም) (4x) በቆዘምኩበት ዘመን ፈንታ ከፍ ሊያደርገኝ ደጉ ጌታ መከራዬንም ሊያስረሳኝ ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ ባለቀስኩበት ዘመን ፈንታ ደግሞ ሊያስቀኝ ደጉ ጌታ መከራዬንም ሊያስረሳኝ ቀኑን ጠብቆ መጣልኝ የካሳ ዘመን አለ ከፊቴ (2x) ልውጣ ልውረሰው ወግድ ጠላቴ ዞርበል ጠላቴ የበቀል ቅባት ስላረፈብኝ ኪዳንህ ፈርሷል ዳግም ላትገዛኝ (2x) ከላይ አዞልኛል የሰማይ አባቴ ሞልቶ እንዲትረፈረፍ በበረከት ቤቴ ከእኔ ይልቅ ለእኔ የሚያስብልኝ አምላክ አላኝና እጅግ ባለጠጋ ለምንስ ልሳቀቅ እንዴት ብዬ ልሥጋ ጠላቴ ሆይ ስማ ብወድቅ እነሳለሁ በጨለማ ብሄድ ጌታ ብርሃኔ ነው የጠራኝ እግዚአብሔር አይጥልም አውቃለሁ እንዳልሰማ የአንተን ስብከት ውሸታም ነህ የውሸት አባት ፈጣሪዬን ለእኔ ልታማ ብዙ ሞከርክ መች ልታቅማማ እኔስ የማውቀው ይሄን ነው እግዚአብሔር ለእኔ መልካም ነው (እግዚአብሔር ለእኔ መልካም) (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection