Song Lyrics

መች ተወኝ

Tewodros Tadesse
Ayamiregnim
አዝ፦ መራመድ ሲያቅተኝ በጽድቅ ጐዳና ነፍሴም ስትጨነቅ በኀጢአት ፈተና ሥጋዬም ሲረክስ ጠፍቶ ህሊናዬ እንደሰው መች ተወኝ (2x) ጌታዬ ጨክኖ መች ተወኝ (2x) ጌታዬ መጠቋቆሚያ ሲያደርገኝ ሰው ሁሉ እንግዲህ ተስፋም የለው እያሉ መች ቀረሁ ወድቄ ተሸማቅቄ ከአምላኬ ጉያ እንዲያው ርቄ እንደገና አረገኝ ቀና እንደገና አረገኝ ቀና (2x) አዝ፦ መራመድ ሲያቅተኝ በጽድቅ ጐዳና ነፍሴም ስትጨነቅ በኀጢአት ፈተና ሥጋዬም ሲረክስ ጠፍቶ ህሊናዬ እንደሰው መች ተወኝ (2x) ጌታዬ ጨክኖ መች ተወኝ (2x) ጌታዬ ምህረትህን የለመደ አመለኛ ተው ቢሉን የማይሰማ እልከኛ ብለው ፈረዱ በእግዚአብሔር ፍቅር በቸርነቱ ብዙ የተረዱ የራሳቸውን ምሶሶ ትተው የሰውን ጉድፍ የሚያዩ አጥርተው (2x) አዝ፦ መራመድ ሲያቅተኝ በጽድቅ ጐዳና ነፍሴም ስትጨነቅ በኀጢአት ፈተና ሥጋዬም ሲረክስ ጠፍቶ ህሊናዬ እንደሰው መች ተወኝ (2x) ጌታዬ ጨክኖ መች ተወኝ (2x) ጌታዬ ይሄ ነው ብዬ የማልጨርሰው ውለታ አለብኝ (2x) ብዙ የማላውቀው ይሄ ነው ብዬ የማልጨርሰው ውለታ አለብኝ (2x) ብዙ የማላውቀው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection