Song Lyrics

አንተ ባለ አደራ

Tewodros Tadesse
Ayamiregnim
እንዲህም አላቸው። ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ። ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ። የማርቆስ ወንጌል ም. ፲፮ ቁ.፲፭ አዝ፦ አንተ ባለአደራ ወዴት ነው ያለኸው የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው አንተ መልዕክተኛ ወዴት ነው ያለኸው የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው ተነስ መጽሓፉን አንሳ ተነስ ሚስጥሩን ግለጠው ተነስ ግራ ለተጋባው ተነስ ልቡን አሳርፈው (2x) የሕይወትን መንገድ አሳየኝ እያሉ በጓዳቸው ሆነው ስንቶች ያለቅሳሉ አሄ አንተ በዳንክበት መዳን አስባቸው የእውነትን ቃል ይዘህ ሂድ ድረስላቸው እህ ሂድ ድረስላቸው ብድራትህን ትኩር ብለህ ተመልከትና የቀድሞው ነገር ትውን ይበልስ እስኪ እንደገና ያኔ የነበረው ትኩስ ፍቅርህ ዛሬም ቢቀና ያቀናልሃል አምላክህ ደግሞ የአንተን ጐዳና አዝ፦ አንተ ባለአደራ ወዴት ነው ያለኸው የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው አንተ መልዕክተኛ ወዴት ነው ያለኸው የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው ተነስ መጽሓፉን አንሳ ተነስ ሚስጥሩን ግለጠው ተነስ ግራ ለተጋባው ተነስ ልቡን አሳርፈው (2x) በሚብለጨለጨው ውበቷ ተማርከው ስንቶች ሲኦል ገቡ ከምድር ተስማምተው አሄ የሰማዩን ክብር የላዩን ሳያውቁ መቃብር ወረዱ ሃያላን አለቁ እህህ ጠቢባን አለቁ ወንጌሉን ይዘህ ሳትመሰክር ዘመን አለፈህ ሰዉ እንደቅጠል በቀን በማታ እየረገፈ መክሊቱን ቀብረህ ሳታተርፍበት ጌታ እንዳይመጣ የተሰጠህን አደራ ይዘህ ፈጥነህ በል ውጣ አሄ አዝ፦ አንተ ባለአደራ ወዴት ነው ያለኸው የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው አንተ መልዕክተኛ ወዴት ነው ያለኸው የወንጌል አርበኛ ሆይ ወዴት ነው ያለኸው ተነስ መጽሓፉን አንሳ ተነስ ሚስጥሩን ግለጠው ተነስ ግራ ለተጋባው ተነስ ልቡን አሳርፈው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection