Song Lyrics

ጌታዬ እኮ ነው

Tewodros Tadesse
Ayamiregnim
አዝ፦ ጌታዬ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው አምላኬ እኮ ነው ይህን ያደረገው ወዳጄ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው ኢየሱሴ እኮ ነው ይህን ያደረገው እንዲህ እና እንዲያ ብዬ የምለው ታሪክ የለኝም ታሪኬ እርሱ ነው(2x) ጠላት እንዳሰበው በእኔ ቢሆንማ የሞት አዋጅ ለቅሶ ነበር በተሰማ(2x) እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት ግን እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት አዝ፦ ጌታዬ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው አምላኬ እኮ ነው ይህን ያደረገው ወዳጄ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው ኢየሱሴ እኮ ነው ይህን ያደረገው እንዲህ እና እንዲያ ብዬ የምለው ታሪክ የለኝም ታሪኬ እርሱ ነው(2x) ያኔ በልጅነት ሳለሁ ብላቴና አሳየኝ በምክሩ የጽድቅን ጐዳና(2x) እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት ግን እንዳልጠፋ እንዳልሞት አስመለጠኝ ከሩቅ አይቶት አዝ፦ ጌታዬ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው አምላኬ እኮ ነው ይህን ያደረገው ወዳጄ እኮ ነው እንዲህ ያደረገው ኢየሱሴ እኮ ነው ይህን ያደረገው እንዲህ እና እንዲያ ብዬ የምለው ታሪክ የለኝም ታሪኬ እርሱ ነው(2x) የማንም እጅ የለበትም እኔስ ለመኖሬ በሕይወት እስከዛሬ (2x) እርሱ ነው ታሪኬ እርሱ ነው አምላኬ እርሱ ነው ኑሮዬ እርሱ ነው ጌታዬ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection