ለእኔስ ሕይወት በዝቶልኛል ሕይወት በዝቶልናል ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል (2x) ሰው ሁሉ እንደመሰለው ቢያወራ ብዙ ቢናገር ለእኔ ግን የገባኝ እውነት አረገኝ በዚያው እንድቀር ለዚህ ነው እምቢ ማለቴ ሳይገደኝ ወጣትነቴ የዓለምን ግብዣዋን ንቄ ወገቤን ትጥቄን ማጥበቄ አዝ፦ አያምረኝም ዛሬ ታይቶ ነገ ሚጠፋ አያምረኝም የዓለም ክብር ጊዜያዊ ተስፋ አያምረኝም ይሄ አይደለም ለእኔማ ክብሬ መኖር እንጂ በእግዚአብሔር ቤት እርሱን አክብሬ (2x) ለእኔስ ሕይወት በዝቶልኛል ሕይወት በዝቶልናል ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል ኢየሱሴ መዳኛ ማምለጫም ሆኖኛል (2x) ትውልዱ ግራ ቢገባው የዘፈን ማዕበል ቢውጠው ነጐደ ፍጥረት ተሰዶ ገንዘብን ዓለምን ወዶ ቀን ሲመሽ ሌቱ ሲነጋ ለአንድ አፍታ ለቤ እንዳይሰጋ የሰማይ ደጆች ተከፍተው የአምላኬን ውበት አያለው አዝ፦ አያምረኝም ዛሬ ታይቶ ነገ ሚጠፋ አያምረኝም የዓለም ክብር ጊዜያዊ ተስፋ አያምረኝም ይሄ አይደለም ለእኔማ ክብሬ መኖር እንጂ በእግዚአብሔር ቤት እርሱን አክብሬ (2x) የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (2x) ሙሉ ልቤ ያረፈብህ የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (2x) ግራ ቀኙን እንዳላየው የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (2x) አንዴ ልቤን የማረከው የዘለዓለም ምርጫዬ ነህ የዘለዓለም (2x)