Song Lyrics

ወደድከኝ

Tewodros Tadesse
Ayamiregnim
ወደድከኝ(3x) እንዲያው ወደድከኝ ወደድከኝ(3x) የፍቅር ነህ እንዲያው ወደድከኝ ታዛዥ አልነበርኩም አመጸና እንቢተኛ እንደልቤ ምኖር ዓለም ወዳድ ዓለመኛ ፍቅርህ ሰው አደረገኝ ወደውስጤ ዘልቆ ገባ ከቅዱሳን ጋራ ሰበሰበኝ እንድልህ አባ አባ ልበል ከወደድከኝ አባ ልበል ከመረጥከኝ አባ ልበል በቸርነትህ አባ ልበል ከደገፍከኝ አባ ልበል ልስገድልህ አባ ልበል ልቀኝልህ አባ ልበል እንዳየህልኝ አባ ልበል ልኑርልህ አባብዬ (2x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ አብትዬ (2x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ ወደድከኝ(3x) እንዲያው ወደድከኝ ወደድከኝ(3x) የፍቅር ነህ እንዲያው ወደድከኝ ሰዎች የናቁትን የገፉትን የረሱትን ሰው ሰው አይሆንም ብለው የተዉትን አንተ ታደከው ዛሬ በአደባባይ ይዘምራል ተቀብቶ የአለፈው ታሪኩ እንዳለፈ ዉሃ ተረስቶ ምን ይባላል ተመስገን እንጂ ምን ይባላል አንተ ስትረዳ ምን ይባላል ፍቅር እኮ ነህ ምን ይባላል የማትከዳ (2x) አባብዬ (2x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ አብትዬ (2x) አንተ እኮ ነህ እድል ፈንታዬ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection