Song Lyrics

አትተወኝ

Tewodros Tadesse
Ayamiregnim
አንዳንዴ ሲከፋኝ ግራ ሲገባኝ መሄጃው ሲጠፋኝ አምላኬ አምላኬ ብዬ እጮሃለሁ ፊትህን እፈልጋለው ዝም አትበለኝ አትተወኝ ረዳቴ የህመሜ ፈዋሽ አንተው ነህና መድሃኒቴ (2x) ምድረ በዳው ሲያንገላታኝ ሃሩሩ ሲያደክመኝ አይዞህ ባይ ሲጠፋ የሚቆም ከጐኔ እምባዬን አፍስሼ ተማጸንኩህ ያኔ አንተም ደረስክልኝ አልጨከንክም በእኔ በመከራዬ ሰዓት የረዳኽኝ በጭንቄ ሰዓት የደረስክልኝ ዛሬም አልሃለሁ ጌታ ሆይ አባክህን አዝ፦ አትተወኝ እያወከው ማንነቴን አትተወኝ እያወከው እኔነቴን አትተወኝ እያወከው ደካማነቴን አትተወኝ እያወከው ውስጤን ጓዳዬን አንዳንዴ ሲከፋኝ ግራ ሲገባኝ መሄጃው ሲጠፋኝ አምላኬ አምላኬ ብዬ እጮሃለሁ ፊትህን እፈልጋለው ዝም አትበለኝ አትተወኝ ረዳቴ (ረዳቴ) የህመሜ ፈዋሽ አንተው ነህና መድሃኒቴ (ዝም አትበለኝ) (2x) ከአንተ ወዴት የት እሄዳለሁ ሚስጥረኛዬ ነህ ከእስትንፋሴ ይልቅ የምትቀርበኝ ጓዴ ዛሬስ መላው ጠፋኝ መግቢያው መውጪያው ሁሉ ድምጽህን አሰማኝ ልሁን እንደቃልህ ያኔ በልጅነቴ ወራት ድምጽህን ለመስማት የነበረኝ ጉጉትና ናፍቆት ዛሬ ግን ከውስጤ ጠፋና ወደአንተ እጮሃለሁ እባክህን (2x) አዝ፦ አትተወኝ እያወከው ማንነቴን አትተወኝ እያወከው እኔነቴን አትተወኝ እያወከው ደካማነቴን አትተወኝ እያወከው ውስጤን ጓዳዬን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection