አዝ፦ አይቶልናል በከፍታ (2x) የመረጠን ጌታ ኧረ አይቶልናል በከፍታ (2x) የመረጠን ጌታ (2x) የምስኪኑ እምባ እንደፈሰሰ መች ቀረ ታዲያ እሄው ታበሰ ዛሬስ ተሰማ እንግዳ ነገር ከጭቁኖቹ ከእነርሱ መንደር ዕልልታ ወጣ አሃሃ ዜማ ፈለቀ አስጨናቂያችን ጐልያድ ወደቀ (2x) [1] አዝ፦ አይቶልናል በከፍታ (2x) የመረጠን ጌታ ኧረ አይቶልናል በከፍታ (2x) የመረጠን ጌታ (2x) ዘመን ሲመጣ ታሪክ ሲቀየር አይተናል እኛ ጌታ ሲያከብር ብለን ዘመርን ተቀኘን ቅኔ በአዲስ ምሥጋና ይዘን በገና ዕልልታ ወጣ አሃሃ ዜማ ፈለቀ አስጨናቂያችን ጐልያድ ወደቀ (2x) [1] አዝ፦ አይቶልናል በከፍታ (2x) የመረጠን ጌታ ኧረ አይቶልናል በከፍታ (2x) የመረጠን ጌታ (2x) ክረምት አለፈ ሃዘን መከራ የድሆች አምላክ ደርሶ ሲራራ ትዕቢተኛውን አዋረደ ለእራሱ ክብር ሲሻ ምሥጋና ዕልልታ ወጣ አሃሃ ዜማ ፈለቀ አስጨናቂያችን ጐልያድ ወደቀ (10x) [1]