Song Lyrics

አስታውሳለው

Tewodros Tadesse
Ayamiregnim
አስተምረኝ ጌታዪ ሆይ አስተካክላት ሕይወቴን መንገዴን ሁሉ ስራመድ አንተ ከእኔ ጋራ ሁን (2x) ክፉና ደጉን ለይቶ ሳያውቀው አስተምረኝ አለ ሌላው እንዳይነካው እንካ ተረከባት ሕይወቴን አደራ በቤትህ አንድኖር አንተን እንድፈራ ልጅነቴን/ጉብዝናዬን ንገሥበት እስከ እርጅና እስከ ሽበት ክበርብኝ ለየኝና ታናሹን የአንተን ብላቴና (2x) መልካም አባት መቼ ይጥላል(2x) ቃልኪዳኑን ይጠብቃል (2x) ታማኝ ነው አደራ ላለው በመንገዱ ለተከተለው ያቆመዋል በቤቱ ተክሎ ያጸናዋል ልጄ ነህ ብሎ (2x) አስተምረኝ ጌታዪ ሆይ አስተካክላት ሕይወቴን መንገዴን ሁሉ ስራመድ አንተ ከእኔ ጋራ ሁን (2x) (አስታውሳለው) ወንድሞቼን እህቶቼን የጨቅላነት ጓደኞቼን (አስታውሳለው) ኧረ አይጠፋም ከአዕምሮዬ የልጅነት ትዝታዬ (አስታውሳለው) ተሰብስበን ስንዘምር አንዱ ለአንዱ ያለው ፍቅር (አስታውሳለው) ክፋት የለ መሀላችን ያ ቅን ዘመን አቤት ሲያምር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection