Song Lyrics

ታሪኬ የጀመረው

Sofia Shibabaw
Sima Belew
ታሪኬ የጀመረው (3x) በመስቀሉ ሥር ነው (2x) የተነሳበትን የማያውቅ የሚደርስበትን አያውቅም የተወለድኩ ቀን ታሪኬ እንደተጀመረ እንኳን ባውቅም ከዚህ ዕውቀት ልኩ ያለፈ ሌላ ዕውቀት ተገልጦልኛል የታሪኬ ጅምር መነሻው ከመስቀሉ ግርጌ ሆኖኛል ያወኩት ቀን አምላኬን ጌታዬ ስቀበለው እንደግል አዳኜ ስመዘገብ በሕይወት መዝገብ ላይ ጀማምረ ታሪኬ እዚያ ላይ (2x) ታሪኬ የጀመረው (3x) በመስቀሉ ሥር ነው (2x) ሰው ሞቶ ሲሸኝ ወደ ቀብር ሁሉም አልቅሶ ይሸኘዋል ቀብረው ሲመለሱ ታሪኩን በቃ ሁሉም ይዘነጉታል የእኔ ግን ከዚህ የተለየ ነው ታሪኬ እዛ ላይ አያበቃም ወደ ዘለዓለማዊው ሃገሬ ጭራሽ ወደ ሌላ ይሻገራል ንፍሴ ከሥጋዬ ስትለያይ ወደ ጌታዋ ስትሄድ ወደ ላይ ሌላ ታሪክ ደግሞ ጀምራለሁ ወደ አዳነኝ ጌታ እሄዳለሁ (2x) ታሪኬ የሚቀጥለው (3x) ከሞት ባሻገር ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection