ያንን ጠያፉን ሕይወት ውበትን ጨምሮበት ሳላውቅ ባለማመን ስላደረኩት አገኘሁ ምህረት (2x) ምንም ብሆን ጌታዬ ምሮኝ ምንም ብሆን ቃሉ አሳምሮኝ ምንም ብሆን ደሙ አሳምሮኝ ደጉ ኢየሱስ ደርሶልኛል ከሰይጣን አፍ አውጥቶኛል ደጉ ኢየሱስ ደርሶልኛል ከጉድ ከእፍረት አውጥቶኛል በምህረቱ ባለጠጋ ኢየሱስ ወደ እኔ ተጠጋ ምንም ብሆን ምንም ብሆን አልጣለኝም ጌታ አለሁ ከእርሱ ጎን (2x) ከቤቴ እንዳትገባ ብዬው የነበረው በፍቅር መጣና ታሪኬን ቀየረው አንድ ሁሉት ተብሎ የሚቆጠር ጽድቄ ምን ነበረኝና ከአብ ፊት ርቄ በመካከል ገብቶ ጠበቃዬ ዋሴ ደጉ ኢየሱሴ ጀርባን ከሚያሰጠኝ ሥራዬ ተሽሮ ዛሬስ እገኛለሁ ቆሻሻዬን ሁሉ ደሙ አሳምሮ ቃሉ አሳምሮ መንፈሱ አሳምሮ ምንም ብሆን ጌታዬ ምሮኝ ምንም ብሆን ቃሉ አሳምሮኝ ምንም ብሆን ደሙ አሳምሮኝ ደጉ ኢየሱስ ደርሶልኛል ከሰይጣን አፍ አውጥቶኛል ደጉ ኢየሱስ ደርሶልኛል ከጉድ ከእፍረት አውጥቶኛል በምህረቱ ባለጠጋ ኢየሱስ ወደ እኔ ተጠጋ ምንም ብሆን ምንም ብሆን አልጣለኝም ጌታ አለሁ ከእርሱ ጎን (2x) የት አለኝ በጐነት የለኝ መልካምነት ልናገር በድፍረት እንዲህ ነው ምልበት የተላለፈብኝ የመርገም ሀረጌ አየሁት በክንዱ ሲሰብረው ጌታዬ እኔነቴን አልፎ ለመጣው ይህ ፍቅር ኧረ እንዴት አልዘምር ምንም ብሆን ይህን አረገልኝ ጌታ እስቲ ላመስግነው ከውስጥ ከመንፈሴ ተሰብሯል ቀምበሬ የድል ቀን ነው ዛሬ ያክብረው ከንፈሬ ምንም ብሆን ጌታዬ ምሮኝ ምንም ብሆን ቃሉ አሳምሮኝ ምንም ብሆን ደሙ አሳምሮኝ ደጉ ኢየሱስ ደርሶልኛል ከሰይጣን አፍ አውጥቶኛል ደጉ ኢየሱስ ደርሶልኛል ከጉድ ከእፍረት አውጥቶኛል በምህረቱ ባለጠጋ ኢየሱስ ወደ እኔ ተጠጋ ምንም ብሆን ምንም ብሆን አልጣለኝም ጌታ አለሁ ከእርሱ ጎን በቃ ልጅ ነኝ እኔ ተሰብሯል ኩነኔ ተጥሏል ከሳሼ ማጥ ውስጥ አልገኝም ዳግም ተመልሼ በምህረቱ ባለጠጋ ኢየሱስ ወደ እኔ ተጠጋ ምንም ብሆን ምንም ብሆን አልጣለኝም ጌታ አለሁ ከእርሱ ጎን (2x)