ኢየሱስን አምኖ የሕይወቱ ጌታ ንጉሱ ያረገ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ጌታን በማመኑ እንደ ሃይማኖት ከጂ አርጐ የተቆጠረ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) ቀድሞ ከነበሩት ከባልንጀሮቹ ተለይቶ ሄደ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ላመነበት ነገር አንገቱን ለካራ ሊሰጥ የጨከነ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) አዝ፦ ደግ አረገ ማለት ደጐ ለሚታየው መልካም ንግግር ነው (2x) በቃላቱ ሳይሆን ፊደሉን ካየነው መልካም ላረገ ነው ደግ ላረገ ነው ለአንዱ ማብሸቂያ ነው ለሌላው እንኳን ነው ለእኔ ደግ አረገ መልካም ንግግር ነው (ደግ አረገ ነው ደግ አረገ ኤይ) ሌሎች እንዲድኑ የምስራቹን ቃል ይዞ የተጓዘ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) በተሰጠው መክሊት ፀጋ እየሰራ ብዙ ያተረፈ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) በስሜቱ ሳይሆን በእግዚአብሔር መንፈስ ውሳኔ ወሰነ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) በዘለዓለም ሕይወት ለሚገኘው አክሊል ሲልም ተሯሯጠ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) አዝ፦ ደግ አረገ ማለት ደጐ ለሚታየው መልካም ንግግር ነው (2x) በቃላቱ ሳይሆን ፊደሉን ካየነው መልካም ላረገ ነው ደግ ላረገ ነው ለአንዱ ማብሸቂያ ነው ለሌላው እንኳን ነው ለእኔ ደግ አረገ መልካም ንግግር ነው (ደግ አረገ ነው ደግ አረገ ኤሂ) ብዙ ምርጫ እያለው አምላኬ መረጠው ይሻለኛል ያለ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ደስታው በእግዚአብሔር ኃይል እንጂ በዚች ዓለም ፈጽሞ ያልሆነ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) ቃል እየተሞላ በከበበው ችግር ላይ እየመዘዘ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ድል በድል የሚሄድ ድካሙን አራግፎ ቆርጦ የተጓዘ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) አዝ፦ ደግ አረገ ማለት ደጐ ለሚታየው መልካም ንግግር ነው (2x) በቃላቱ ሳይሆን ፊደሉን ካየነው መልካም ላረገ ነው ደግ ላረገ ነው ለአንዱ ማብሸቂያ ነው ለሌላው እንኳን ነው ለእኔ ደግ አረገ መልካም ንግግር ነው (ደግ አረገ ነው ደግ አረገ ኤሂ) ሰው ሲያስቀይመው ምህረትና ይቅርታ ለሁሉ ያረገ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) በቀል የእግዚአብሔር ነው ብሎ ሁሉን ትቶ ለፍቅር የኖረ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) ህሊናው የጸዳ በሰዎች ጉዳይ ውስጥ ገብቶ ያልፈተፈተ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ሁሉን ሰው የሚያውቀው በክርስቶስ ብቻ በሌላ ያልሆነ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) አዝ፦ ደግ አረገ ማለት ደጐ ለሚታየው መልካም ንግግር ነው (2x) በቃላቱ ሳይሆን ፊደሉን ካየነው መልካም ላረገ ነው ደግ ላረገ ነው ለአንዱ ማብሸቂያ ነው ለሌላው እንኳን ነው ለእኔ ደግ አረገ መልካም ንግግር ነው (ደግ አረገ ነው ደግ አረገ ኤሂ) ምሥጋና ለመስጠት መስዕዋት ለማቅረብ ወደኋላ ያላለ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ከማንም ከምንም አምላኩን ለማክበር እራሱን የሰጠ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) ውለታ የማይረሳ ድንቅ ተዓምራቱን ለሁሉ የነገረ (ደግ አረገ ኤኤ ደግ አረገ) ሁልጊዜ ምሥጋና ከአፉ የማይጠፋ ዕልልታን ያወቀ (ደግ አረገ ኤሂ ደግ አረገ) አዝ፦ ደግ አረገ ማለት ደጐ ለሚታየው መልካም ንግግር ነው (2x) በቃላቱ ሳይሆን ፊደሉን ካየነው መልካም ላረገ ነው ደግ ላረገ ነው ለአንዱ ማብሸቂያ ነው ለሌላው እንኳን ነው ለእኔ ደግ አረገ መልካም ንግግር ነው (ደግ አረገ ነው ደግ አረገ ኤሂ)