ሆ (8x) ህዝቡን ከባርነት ፈልቅቆ ያወጣ ከድንጋይ ላይ ውኃን አፍልቆ ያጠጣ በመሪባ ውኃ ያረሰረሳቸው በሲና ተራራ ያነጋገራቸው አምላካችን እርሱ ሥሙም እግዚአብሔር ነው እግዚአብሔርን እንወደዋለን (4x) ሙዚቃውን ስትሰሙ ለቆመው ለምስጉን ለአምላኬ ወድቃችሁ ስገዱ ሲባሉ እንኳንስ ሊሰግዱ ቢንቀለቀል ቶኑ ፈፁም ፍንክች አይሉም ሶስቱም ከጨከኑ ከአምላካቸው ሌላ ለማንም አይሰግዱ [1] ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ አናውቅም ከእርሱ በቀር ሌላ አናመልክም ለአምላካችን እንሰግድለታለን ለእግዚአብሔር እንሰዋለታለን አንሰዋም ለባዳን አማልክት አንሰግድም ለሠማይ ሠራዊት ስግደትን ስግደት ለሚገባው ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው (2x) ገና ያኔ ገና ሠማይ ምድርን ሲሰራ (ኡ ኦ ኡ ኦ) ቀላያትን ሲቀድ ብርሃንን ሲያበራ (ኡ ኦ ኡ ኦ) ይሁን ያለው ሁሉ ሁሉ ለሆነለት ክብር ይሁን ክብር ለፍጥረታት አባት ለአምላካችን ለእርሱ ለፈጠረን ጌታ ዘለዓለም ይድረሰው ክብርም ምሥጋና (2x) ሆ ብለን እንሄዳለን እናመልከዋለን ሆ ብለን እንሄዳለን እንሰግድለታለን (4x) አንሰዋም ለባዳን አማልክት አንሰግድም ለሠማይ ሠራዊት ስግደትን ስግደት ለሚገባው ለልዑል እግዚአብሔር ብቻ ነው (2x) ሆ ብለን እንሄዳለን እናመልከዋለን ሆ ብለን እንሄዳለን እንሰግድለታለን (4x)