ሰው ማነህ አይባል ሳይባል ነኝ ይላል ከስሙ አስቀድሞ ያለ የሌለ ነገር ጨማምሮ ይናገራል ሥራህስ ምንድን ነው ብለው ቢጠይቁት አሳምሮ ያወራል ያብራራል ከሰሙት ለመጥምቁ ዮሐንስ ኢሄ እድል ደረሰው አንተ ማነህ ብሎ ብዙ ህዝብ ጠየቀው እንዲህ ሲል መለሰ ስለ ማንነቱ ሳያፍር ገለጠ እውነትን ከውሸቱ እኔ ጠራጊ ነኝ ድምጽ ነኝ ምጮኸው መንገድ የማዘጋጅ ከኋላ ሄዳለሁ አይደለሁም ኤልያስ ከነብያቶች አንዱ የማመቻች ነኝ ጥርጊያ ለመንገዱ አላቸው መልሶ ራሱን አሳንሶ የጫማውን ጥፍር ልፈታ የማይገባኝ ከእርሱ አንሳለሁኝ እኔ ላንስ ይገባል እርሱ ከእኔ ይበልጣል እኔ በውኃ ሳጠምቅ በእሳት ያጠምቃል እርሱ ከእኔ ይበልጣል[1][2] እንዲህ ነው እንግዲህ ትህትና እንዲህ ነው እንግዲህ ዝቅ ማለት (2x) ራስን ማወቅ ማንነትን ሰው መሆንን መረዳትን ያበዛዋል መዋረድን ሒሳቡ ደግሞ ኢሄ ነው ዝቅ ያለ ነው ከፍ የሚለው (2x) እኔ (6x) ባልኩኝ ቁጥር እወጣለሁኝ ካለሁበት አጥር እኔ (6x) ያልኩኝ ለታ ያበቃልኛል የማታ የማታ እኔነቴ መድከሚያዬ እኔነቴ መውደቂያዬ እኔነቴ መወጫዬ እኔነቴ መቃብሬ ስንቱ ተቀበረ በእኔነት መቃብር ትንሳዔ ያምጣለት ትሁቱ እግዚአብሔር (2x) እንደ እንጀራ አይለመን ትህትና መለወጥ ነዉ መወሰን ነዉ የሚያስፈልገዉ በትዕቢት ከጋሉ እኔነቴ መድከሚያዬ እኔነቴ መውደቂያዬ እኔነቴ መወጫዬ እኔነቴ መቃብሬ