የእኔን ሰው መሆን የፍጥረቴን ሚስጥር የደመነፍስ ኑሮን ጠፍቶ የሚተረትር የታረደለኝ በግ ትርጉም ያለው ሕይወት ያለኝ ነገር እኔም ዝቅ በዬ ልስገድለት ለእርሱ ምሥጋና ነው ያለኝ ምሥጋና (4x) ነው ያለኝ (2x) ተከተይኝ አለኝ ትምክቴን አስጥሎ የዓለም አይደለሽም አንቺ የእኔ ነሽ ብሎ አክብሮት አምልኮ ለሌላው ለመስጠት ጉልበቶቼ ታጥፈው ሊንቀጠቀጡለት እንዲህ አይደረግም (2x) ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም (2x) ያልሳሳ ገበታን ጌታዬ አዘጋጅቶ ከሕይወት ቃል ማዕድ መንፈሴን አርክቶ እንዳዜም ካበቃኝ በሕያዋን ምድር ልሰግድ ይገባኛል ከንጉሡ እግር ሥር ይገባኛል (2x) አምላኬ እኮ እኔን ሌላ ሰው አርጐኛል (2x) ከምድራዊው ኑሮ ያለፈ አለ ብሎ የሞተልኝ ጌታ የእኔን እዳ ከፍሎ ክርስቶስን ለበስኩ እንዴት አምሮብኛል ክብሬና ሞገሴን ማን ያወልቅብኛል እንዲህ አይደረግም (2x) ጌታዬ ልዩ ነው ማንንም አይመስልም (2x) የእኔን ሰው መሆን የፍጥረቴን ሚስጥር የደመነፍስ ኑሮን ጠፍቶ የሚተረትር የታረደለኝ በግ ትርጉም ያለው ሕይወት ያለኝ ነገር እኔም ዝቅ በዬ ልስገድለት ለእርሱ ምሥጋና ነው ያለኝ ምሥጋና (4x) ነው ያለኝ ዕልልታ (4x) ነው ያለኝ (2x)