የእኔ ምሥጋና ዝናብ እንደሌለው ደመና ውኃ እንደሌለው ደመና አይደለም የእኔ ምሥጋና (2x) ወይ ዘንቦ ላይዘንብ ወይ ጥሎ ላይጥል መብረቁ ሲያስፈራ ሲል ብልጭ ድርግም (፪×) ነጐድጓዱ ታሞ ጠብ እንኳን ካላለ ዝናብ ፈርቶ ሰው ቤቱ ከዋለ ተታለለ ግርግር ባይኖር ሙዚቃ ባልሰማ የነፍሴ ምሥጋና ዙፋኑ ይሰማ ዝናብ እንደሌለው ደመና አይደለም የእኔ ምሥጋና የእኔ ምሥጋና ዝናብ እንደሌለው ደመና ውኃ እንደሌለው ደመና አይደለም የእኔ ምሥጋና እህሉ ሊበላሽ ዘንቦበት በረዶ እያለ ሲያወራ ካሁን አሁን ወርዶ በረዶ ጉሙ ሲያጉረጐርም መጣሁኝ እያለ ደመናው ሰንጥቆት ፀሐይ ብቅ ካለ ተታለለ ዝም ብዬ የምጮህ እንዲያው ባዶ ሜዳ አይደለሁም እኔስ ሞልቶኛል ምሥጋና ዝናብ እንደሌለው ደመና አይደለም የእኔ ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና (2x) እሰዋለሁ ለጌታዬ ለአምላኬ ይገባዋልና በከፍታ በዝቅታ አምልኮዬን አቀርባለሁ ለእርሱ ክብር በደስታ ምሥጋና ምሥጋና (2x) ለጌታዬ ለታደገኝ ለአዳነኝ ለክብሩ ዝቅ እያልኩኝ እየሰገድኩ እያመለኩ ፊቱ ብወድቅ ባደንቀው ባሞግሰው ለእርሱ አይበቃም የእኔ ምሥጋና ዝናብ እንደሌለው ደመና ውኃ እንደሌለው ደመና አይደለም የእኔ ምሥጋና (2x)