Song Lyrics

ይገባ ነበር ዎይ

Sofia Shibabaw
Sima Belew
ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ [1][2] ይገባ ነበር ዎይ ስለ እኔ ማልቀስህ ይገባ ነበር ዎይ እንዲያ መዋተትህ ይገባ ነበር ዎይ መስቀል ላይ መሞትህ ዎይ (፲3x) ይዘዉህ ሲሄዱ እንደሚታረድ በግ ዝም ብለህ እየሄድክ አንዳች ሳትሟገት ማነኝ ለመሆኑ እንዴት እወደድከኝ ከክብር ላይ ወርደህ የተዋረድክልኝ አቤቱ ፍቅርህ ጥልቀቱ አቤቱ መውደድህ ስፋቱ አይመረመርም በሰው ዘንድ ታላቅ ነው ጌታ የአንተ መውደድ ፊቴ ድቅን ይላል የእሾህ ጉንጉኑ የጅራፉ ብዛት የገላ ሰንበሩ ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ [1][2] ብለህ ስትጨነቅ ስለእኔ ስትሞት ግን አቤቱ ፍቅርህ ጥልቀቱ አቤቱ መውደድህ ስፋቱ አይመረመርም በሰው ዘንድ ታላቅ ነው ጌታ የአንተ መውደድ ይገባ ነበር ዎይ ጻድቅ አይደለህ ዎይ ይገባ ነበር ዎይ ንጹህ አይደለህ ዎይ ጻድቅ ሰው በመስቀል እርቃኑን አደረ ስለ ኃጥያተኞች ደሙን አፈሰሰ ይገባ ነበር ዎይ ስለ እኔ ማልቀስህ ይገባ ነበር ዎይ እንዲያ መዋተትህ ይገባ ነበር ዎይ መስቀል ላይ መሞትህ ዎይ (፲3x) አቤቱ ፍቅርህ ጥልቀቱ አቤቱ መውደድህ ስፋቱ አይመረመርም በሰው ዘንድ ታላቅ ነው ጌታ የአንተ መውደድ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection