Song Lyrics

አምላኬ

Sofia Shibabaw
Sima Belew
ሃፍረት አስቀርቅሮ አንገቴ ላይ ቀና የበደሌ ቀንበር በላዬ ባሰና በቀራንዮ ላይ ባፈሰስከው ደምህ ድፍረት ሆኖልኛል እንድቆም በፊትህ አዝ፦ አምላኬ አምላኬ (3x) ክብሬ ነህ ማዕረጌ (2x) ሥምህን ጠርቼ ድኛለሁኝና (አምላኬ) በላይ በላዩ ላይ ልደርብ ምሥጋና (አምላኬ) ኧረ እኔ አመለጥኩኝ አንተን በማመኔ (አምላኬ) በሰውነቴ ላይ ታወቀኝ መዳኔ (አምላኬ) ታድያ እንዴት ዝም ይላል የተደረገለት (አምላኬ) በድግድግ ጨለማ ብርሃን የሆንክለት (አምላኬ) አዝ፦ አምላኬ አምላኬ (3x) ክብሬ ነህ ማዕረጌ (2x) አንተን በመምረጤ አላፈርኩም ከቶ ሰላም ሆኖልኛል ቃልህ ልቤ ገብቶ መታመኛዬ ነህ ኮርቼብሃለሁ በሕይወቴ ዘምን አንተን አመልካለሁ አዝ፦ አምላኬ አምላኬ (3x) ክብሬ ነህ ማዕረጌ (2x) ስገጅ ስገጅ አለኝ ተገርፈሃልና (አምላኬ) ልሰጥ የሚገባኝ ይኸው የእጅ መንሻ (አምላኬ) ግሩም የዕርቅ ቀን ስለሆነ ለእኔ (አምላኬ) ምሥጋናዬ ኢኸው ይፈሳል ከልቤ (አምላኬ) ከጻድቃን ማህበር እኔም ልቀላቀል (አምላኬ) ለዚህ በቅቻለሁ ለክብር ልታሰብ (አምላኬ) አዝ፦ አምላኬ (አምላኬ) አምላኬ (አምላኬ) (3x) ክብሬ ነህ ማዕረጌ (3x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection