ስለ ጻድቅ ሰው የሚሞት በጭንቅ ቢገኝ እንዴት ተገኘ ብዬ አያስደንቀኝ ስለ ቸር ሰው ቢሆን እንደዚሁ ነኝ እኔ ጊዜዬን በዚህ አልፈጅም ለምኔ ለምኔ አንድ ነገር አለ እኔን ያስደነቀኝ ደካማ እያለሁ ሳላውቀዉ ያወቀኝ ሃጥያት ያራቀኝ ከመንገድ አውጥቶ ኢየሱስ መለሰኝ ሞቴን ሁሉ ሞቶ አሃ አዝ፦ እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (2x) በአንዷ አለመታዘዝ ብዙዎች ኃጥያተኛ ሆኑ [1] ከዲያብሎስ ጋራ ገሃነም ሊጣሉ በኢየሱስ መታዘዝ ከፍርድ አምልጠናል [2] የመንግሥተ ሠማይ ወራሽ አድርጐናል አዝ፦ እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (2x) ዝቅ ዝቅ ያለው ኢየሱስ ከሁሉ ይበልጣል ለእኔ ባረገው ነገር ልቤ ተሸንፏል የፍቅርንም ሚስጥር ያወኩት በእርሱ ነው አቀብት ዳገቱን የወጣዉ ለእኔ ነው በደሙ ፀድቄ ከቁጣ ድኛለሁ ጠላትነት ቀርቶ ወገን ተብያለሁ ሰላሙን ሰብኮኛል የሰላም አለቃ የጭንቀቱ ዘመን ከእኔ ላይ አበቃ አሃ አዝ፦ (እንዴት ያለ ፍቅር ነው) እንዴት ያለ ፍቅር ነው ንፍስን የሚያሰጠው እንዴት ያለ መውደድ ነው እንዲህ የሚያስወደው (4x)