በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ከአንተ ጋር እንደመኖር በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ከአንተ ጋር እንደመኖር እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×) ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤ በአንተ ዘንድ ያለ የህይወት ቃል ሌላ ስፍራ የትም 'ማላገኘው ብር የማይሰጠኝ ወርቅ የማይሰጠኝ የሕይወቴን አቅጣጫ የለወጠው፤ የሁልጊዜ ነው የልቤ ሰላም ከመንፈስህ ከቃልህ የመነጨው በዚህ አለም ነገር የማይወሰን የእኔን ሕይወት የደስታ ያደረገው ብዙ ደስታ አለ በሕይወቴ ብዙ ደስታ አለ፤ ብዙ ሰላም አለ በሕይወቴ ብዙ ሰላም አለ፤ ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ ሸክም የከበደው ወደ እኔ ይምጣ ይረፍ ብለህ የጠራኸኝ አንተ እኮ ነህ ሁሉንም ነገር ለአንተ ሰጥቼ እፎይ ብዬ ተደላድዬ ምኖርብህ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ያለኝ ህብረት ማለት ለእኔ አለሜ ነው፥ አለሜ ነው ለሕይወቴ ትርጉም ያገኘሁበት ምክንያቱ ነው የዘላለሜ የሰመረበት በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ከአንተ ጋር እንደመኖር በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ከአንተ ጋር እንደመኖር እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ እወደዋለሁ ሕይወቴን እወደዋለሁ እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ ሳስበው ካ'ንተ ጋር እንዳለሁ (3×) ሳስበው ሁሌ እደሰታለሁ፤