Song Lyrics

ኢየሱስ አንተን በማመኔ

Samuel Negussie
Beegziabher Alem
የከፍታ ዘመን የብርሃን ሕይወት የሚጨምር ሰላም የሚጨምር ደስታ የክብር ዘመን ነው ከፊቴ ያለው መልካሙን አዋጅ እኔ አውጃለው ጨለማው አልፎ ያለቀስኩበት ዛሬ ብርሃን ሆንዋል ኧረ በእኔስ ሕይወት አለም ሁሉ ይስማ ይህን ይወቅልኝ ምክንያቱም ይሄ ነው ኢየሱስ ስላለኝ ኢየሱስ አንተን በማመኔ (3x) ኢየሱስ አንተን በማመኔ (3x) ባርነቴ ቀርቶ ወራሽ ሆንኩ እኔ ወራሽ ሆኛለው ወራሽ ሆኛለው (2x) ወራሽ ሆኛለው ወራሽ ሆኛለው አሄ ወራሽ ሆኛለሁ ልጅህ ሆኛለሁ ይኸው በደስታ አንተን አመልካለው ስላምና ደስታ ዕረፍት ሆነ ቤቴ መዳኔ ዕውን ሆነ ሳስገባው ወደ ቤቴ ነፃነቴን ላውጅ ከግዞት መውጣቴን በብርሃን አለም ከአንተ ጋር መሆኔን ከእንግዲ ጨለማ በእኔ ሕይወት የለም ሞት መውጊይው ተሰብርዋል እኔን አይነካኝም እርግማኔን ሽረህ ፅድቅን አለበስከኝ በማመኔ ብቻ ወራሽ አደረከኝ ኢየሱስ አንተን በማመኔ (3x) ኢየሱስ አንተን በማመኔ (3x) ባርነቴ ቀርቶ ወራሽ ሆንኩ እኔ ይሁንልህ ምሥጋና ይሁንልህ ዝማሬ ይሁንልህ አምልኮ ይሁንልህ ጌታዬ (2x) ከሞት ድኛለሁና ከሞት ድኛለሁና ከሞት ከሞት ድኛለሁና ላንተ ምስጋና የደም ነው ኪዳኑ የተሳሰርንበት ከፍሎልኛል ዋጋ ያንድ ልጁን ህይወት ሆኖኛል አባቴ እኔም ደግሞ ልጁ ወራሽ አድርጎኛል የሰማይ የምድሩ የክብር የከፍታ የደስታ መሆኑን አረጋግጫለው የቀረው ዘመኔን ድል በነሳው የሱስ ድልን ስላገኘው ከንግዲህ ህይወቴ ላንተ መዘመር ነው ባንተ ታሰበ የዘላለሜ ቀረ ባርነት ነፃ ሆንኩ እኔ ዛሬ በደስታ እዘምራለው የሰማይ ዜጋ ወራሽ ሆኛለው ወራሽ ሆኛለው ወራሽ ሆኛለው (2x) ወራሽ ሆኛለው ወራሽ ሆኛለው አሄ ወራሽ ሆኛለሁ ልጅህ ሆኛለሁ ይኸው በደስታ አንተን አመልካለው ይሁንልህ ምስጋና ይሁንልህ ዝማሬ ይሁንልህ አምልኮ ይሁንልህ ጌታዬ ይሁንልህ ዕልልታ (3x) ይሁንልህ ለጌታ ይሁንልህ ምሥጋና ይሁንልህ ዝማሬ ይሁንልህ አምልኮ ይሁንልህ ላምላኬ ከሞት ድኛለሁና ከሞት ድኛለሁና ከሞት ከሞት ድኛለሁና ላንተ ምስጋና
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection