በስጋም በነፍስም የባረከኝ (2x) ደጋግሞ የባረከኝ በልጁ በኢየሱስ የባረከኝ (2x) ደጋግሞ የባረከኝ ጌታ አልበቃህም ወይ ባርከኽኝ (2x) እኔ እንኳን ብል በቃኝ አንተ መቼ እረካህ ባርከኽኝ (2x) እኔ እንኳን ብል እፎይ ሀዘን የሌለበት በረከት ደስታ ብቻ የሆነ ኢየሱስን ሰጥተህ ባርከህኛል በል ሂድ ልጄ ብለህ ሀዘን የሌለበት በረከት ደስታ ብቻ የሆነ ኢየሱስን ሰጥተህ ባርከህኛል ተከናወን ብለህ በረከቴ ኢየሱስ ነው በረከቴ ኢየሱስ ነው (3x) በረከቴ እራሱ ነው በረከቴ ማንነቱ ነው አንዴ የሚወጣ ተመልሶ ደግሞ አንዴ የሚወርድ አይደል በረከቴ በምድር እንዳለው የሚመጣ የሚሄድ ኢየሱስን ሰጥተህ አንዴ ዘላለሜን አባ ባርከኽዋል እጠቀመዋለው መንዝሬ መንዝሬ እንኳን ለእኔ ለአለም ሁሉ ይበቃል በረከቴ ኢየሱስ ነው በረከቴ ኢየሱስ ነው (3x) በረከቴ እራሱ ነው በረከቴ ማንነቱ ነው በሰማዩ ስፍራ በመንፈሳዊ ሁሉ በረከት ባረከኝ በልጁ በኢየሱስ ሥምም ስላመንኩኝ ሁሉን አወረሰኝ የእርሱን በጐነት የእርሱን መልካምነት ለዓለም አወራለው በረከቴ ኢየሱስ የጐደለኝ የለም አንተን ስላገኘው የኔማ የኔማ በረከት ሰላም የሞላበት ደስታ የሞላበት ኢየሱስ ያለበት የእኔማ የእኔማ በረከት የተትረፈረፈ ፈጽሞ የማያልቅ ኢየሱስ ያለበት ኢየሱስ ያለበት (7x) ሰላም የሞላበት ኢየሱስ ያለበት (7x) ኢየሱስ ያለበት በረከቴ ኢየሱስ ነው በረከቴ ኢየሱስ ነው (3x) በረከቴ እራሱ ነው በረከቴ ማንነቱ ነው