በዚህ ዓለም ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ከአንተ ጋር አንደመኖር በዚህ ምድር ምን ደስ የሚያሰኝ ነገር አለ ከአንተ ጋር አንደመኖር እወደዋለሁ ሕይወቴን የለወጠው እወደዋለሁ መኖሬን እወደዋለሁ በአንተ ዘንድ ያለን የህይወት ቃል ሌላ ስፍራ የትም ማላገኘው ብር የማይሰጠኝ ወርቅ የማይሰጠኝ የሕይወቴን አቅጣጫ የለወጠው የሁልጊዜ ነው የልቤ ሰላም ከመንፈስህ ከቃልህ የመነጨው በዚህ አለም ነገር የማይወሰን የእኔን ሕይወት የደስታ ያደረገው ብዙ ደስታ አለ በሕይወቴ ብዙ ሰላም አለ በሕይወቴ ጌታ ኢየሱስ ከእኔ ጋር ስላለ መንፈስ ቅዱስ በእኔ ውስጥ ስላለ ሸክም የከበደው ወደ እኔ ይምጣ ይረፍ ብለህ የጠራኸኝ አንተ እኮ ነህ ሁሉንም ነገር ለ አንተ ሰጥቼ እፎይ ብዬ ተደላድዬ ምኖርብህ ኢየሱስ ከአንተ ጋር ያለኝ ህብረት ማለት ለእኔ አለሜ ነው ለሕይወቴ ትርጉም ያገኘሁበት ምክኒያቱ ነው የዘላለሜ የሰመረበት