አዝ፦ በዛ ለእኔስ በዛ ምህረትህ በዛ በዛ ለእኔስ በዛ ቸርነትህ በዛ በዛ ለእኔስ በዛ በጐነትህ በዛ በዛ ለእኔስ በዛ ምህረትህ በዛ አገር መርጬ ተናግሬአለሁ በማንነትህ ስለተመካሁ ሁሉ በሁሉ የሆነ አባት አለኝ ልዩ የምልበት ሆነህ አግኝቼሃለሁ ከእስትንፋሴ ቀርበህ ከምልህም በላይ ጌታዬ ልዩ ነህ (2x) አዝ፦ በዛ ለእኔስ በዛ ምህረትህ በዛ (2x) በዛ ለእኔስ በዛ ቸርነትህ በዛ በዛ ለእኔስ በዛ ቸርነትህ በዛ ስሜ ተፅፎ በሕይወትህ መዝገብ የምጽዓት??? ሰው በምድር ስታስብ መጽዓተኝ ሰው መሆኔን ሳውቀው የጌታዬ ጣት ጓዳዬን ሞላው በስብከት ሞኝነት የወደድኩት ጌታ በፍቅሩ ማረከኝ መጥቶ በዝግታ በስብከት ሞኝነት የመረጥኩት ጌታ የእራሱ አደረገኝ መጥቶ በዝግታ አዝ፦ በዛ ለእኔስ በዛ ፍቅርህ በዛ (2x) በዛ ለእኔስ በዛ ምህረትህ በዛ በዛ ለእኔስ በዛ በጐነትህ በዛ ያለ ኢየሱስ ራቁቱን ቆሞ ፈውስ ይላል ቃል ገጣጥሞ ወግ ማዕረግ ረስቶ ፍፁም እርካታ በኢየሱስ ብቻ ሰላም አፎይታ የተገረማችሁ በሚያስገርም ጌታ ደስታችሁን ግለጹ በሆታ በደስታ (2x) የተደነቃችሁ በሚያስደንቅ ጌታ ደስታችሁን ግለጹ በሆታ በዕልልታ (2x) አዝ፦ በዛ ለእኔስ በዛ ቸርነትህ በዛ (2x) በዛ ለእኔስ በዛ በጐነትህ በዛ በዛ ለእኔስ በዛ ቸርነትህ በዛ ሃሌሉያ አሜን