አዝ፦ ምሥጋና ተሞልታለች ነፍሴ (2x) አቀርብልሃለሁ ክብርና ውዳሴ ቸርነትህ ብዙ ውዱ የእኔ ጌታ አጐናጽፈኸኛል የዘለዓለም ደስታ ተረስቻለሁ ጌታ ትቶኛል የተጣልኩኝ ነኝ ማን ያስበኛል ብዬ ሳነባ የራራህልኝ ተመስገን ጌታ ኢየሱስ ስላስታወስከኝ አዝ፦ ምሥጋና ተሞልታለች ነፍሴ (2x) አቀርብልሃለሁ ክብርና ውዳሴ ቸርነትህ ብዙ ውዱ የእኔ ጌታ አጐናጽፈኸኛል የዘለዓለም ደስታ ቤት የሌለው ሰው ሆኜ ከርታታ ያደላደልከኝ የእረፍቴ ጌታ ለልቤ ትምክህት ስለሆንክልኝ ከፍ በል ውዱ አምላኬ ስላከበርከኝ አዝ፦ ምሥጋና ተሞልታለች ነፍሴ (2x) አቀርብልሃለሁ ክብርና ውዳሴ ቸርነትህ ብዙ ውዱ የእኔ ጌታ አጐናጽፈኸኛል የዘለዓለም ደስታ ባዶ ሕይወቴን በዘይት ሞልተህ የነፍሴን ጥማት ከእጅህ አርክተህ በፍቅርህ ስበህ ሰው ስላረከኝ ተባረክ የእግዚአብሔር ልጅ ስለባረከኝ አዝ፦ ምሥጋና ተሞልታለች ነፍሴ (2x) አቀርብልሃለሁ ክብርና ውዳሴ ቸርነትህ ብዙ ውዱ የእኔ ጌታ አጐናጽፈኸኛል የዘለዓለም ደስታ አንተ ጌታዬ ሁሌ በምክርህ ሰው እንዳይጠፋ ነውና ሃሳብህ በሕይወት ቃልህ ልቤን አፀናህ ከፍ በል በምድር ይግነን ክብርህና ዝናህ አዝ፦ ምሥጋና ተሞልታለች ነፍሴ (2x) አቀርብልሃለሁ ክብርና ውዳሴ ቸርነትህ ብዙ ውዱ የእኔ ጌታ አጐናጽፈኸኛል የዘለዓለም ደስታ