Song Lyrics

በማለዳ

Samuel Borsamo
Begeta Hulu Yichalal
አዝ፦ በማለዳም ምሥጋና በቀትርም ምሥጋና በሌሊትም ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ይገባሃልና (2x) ከየቀኑ ክፋት ስምህ ታድጐን በቁሳቁስ ብዛት??? ልጅህ??? ተጥሎ ከሚርመሰመሰው ከአመጽ ጦር ተዋግተህ አሸንፈን ኢየሱስ አለን ከአንተ ጋር አዝ፦ በማለዳም ምሥጋና በቀትርም ምሥጋና በሌሊትም ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ይገባሃልና (2x) ሃዘንን በደስታ ጥማት በርካታ ርሃብን በጥጋብ ጭንቀት በእፎይታ ሁሉንም በጊዜው ውብ አድርገህ የሰራህ የዘለዓለም አምላክ ኢየሱስ ይባረክ ስምህ አዝ፦ በማለዳም ምሥጋና በቀትርም ምሥጋና በሌሊትም ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ይገባሃልና (2x) ትንሿ አንደበቴ ምን ብላ ታውራ አሳልፈኸኛል ጽኑውን መከራ ውለታህ ያለበት ቆሞ ያመስግንህ ሌላ ምን ልበልህ አንተ ክብሩ ነህ አዝ፦ በማለዳም ምሥጋና በቀትርም ምሥጋና በሌሊትም ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ይገባሃልና (2x) ስለ ታላቅ ስራህ የምለው አለኝ በምክርም በድንቅ በሳቅ ሞላኸኝ ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ድረስ ዙፋንህ ከፍ ይበል ውዴ አንተ ተወደስ አዝ፦ በማለዳም ምሥጋና በቀትርም ምሥጋና በሌሊትም ምሥጋና ምሥጋና ምሥጋና ይገባሃልና (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection