አዝ፦ ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ አሰላስላለሁ የጌታን በጐነት በእኔ ላይ ያለውን የአላማውን ፅናት ጌታ አስደንቆኛል አመስግን ይለኛል ምህረቱን ልዘምር በእርግጥ ይገባኛል ማዳኑን ልናገር በእርግጥ ይገባኛል (2x) አዝ፦ ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ ሲጣሉ ብቻቸው ሲታዩ ግን በዙ ከእሳት የሚታደግ ማን ይሆን ጐበዙ የነገሥታት ንጉሥ የኃያላን ሃያል በምስሉ ላይሰግዱ ከሚጨክኑት ጋር ይቆማል እግዚአብሔር ስሙን ሊያስከብር ጌታ አስደንቆኛል አመስግን ይለኛል ምህረቱን ልዘምር በእርግጥ ይገባኛል ማዳኑን ላወራ በእርግጥ ይገባኛል አዝ፦ ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ በአርጤክስስ ዘመን የሞት አዋጅ ወጣ ኃይሉ እንዲወገድ ፍቅሩ??? እንዲታጣ አዋጁን ለወጠው ሞትን ገለበጠው ከላይ ተፈርዶበት ጽዋውን ጨለጠው እግዚአብሔር ተዋጊ ስሙም እግዚአብሔር ነው ጌታ አስደንቆኛል አመስግን ይለኛል ምህረቱን ልዘምር በእርግጥ ይገባኛል ማዳኑን ልናገር በእርግጥ ይገባኛል (2x) አዝ፦ ጌታ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ኢየሱስ አበረታኸኝ አጠገቤ ቆሞ ፈጥኖ ደረሰና ከክፉ ፊት ቀድሞ ነፍሴን ከሚዋጋ ከክፉ ፊት ቀድሞ