ደስታችን በምድር ፍፁም ባይሆን እንኳን ልባችን ሲመታ በመከራ ሃዘን የጌታን መገለጥ በመጠበቃችን የምንጽናናበት አዲስ አገር አለን አዝ፦ ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን በገዛ ዙፋኑ በቀኝ ሊያስቀምጠን የምድር መጽዐተኛ ባለ ፅኑ ተስፋ በላይ ያለው ሽቶ በምድር የተገፋ ባይደላውም እንኳን ፀንቶ በመታገስ በክብር ያየዋል የናፈቀውን ንጉሥ አዝ፦ ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን በማያልፈው መንግሥት ዘለዓለም ሊያነግሰን የዚህን ዓለም ሃሳብ ታግሎ ያሸነፈ በመከራ ፀንቶ በትዕግሥት ያለፈ አምላኩ ሲገለጥ እጅጉን ይፅናናል ያልተሰማ ዜማን ውዳሴን ያፈልቃል አዝ፦ ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን በማያልፈው መንግሥት ዘለዓለም ሊያነግሰን መከራም ይረሳል ሃዘንም ይቀራል ያናዝሬቱ ኢየሱስ እምባችንን ያብሳል ጻድቅ ፈራጃችን በቅርብ ይገለጣል የወጉትም ዐይኖች ፊት ለፊት ያዩታል አዝ፦ ተንቀን አንቀርም ተጥለን በምድር አዲስ አገር አለን ከአድማስ ባሻገር ጌታም ይመለሳል ዳግም ሊያሳርፈን በገዛ ዙፋኑ በቀኝ ሊያስቀምጠን (2x)