አዝ፦ ይቻላል አዎን ይቻላል ይቻላል በእርግጥ ይቻላል በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (2x) ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል በጌታ ሁሉ ይቻላል (2x) ሰላሳ ስልሳ መቶ የክፉን ሃይል አጥፍቶ ለአምላክ ይቻላል ለአባት ይቻላል ከልካዩን ልከለክል አዳኙን ልናድነው ስሙ ሃያል ነው ስሙ ሃያል ነው ችሎ የሚያስችለኝ ጌታ እያለኝ ለምን ስንፍናን አወራለሁኝ አዝ፦ ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል በጌታ ሁሉ ይቻላል (2x) የቀደሙት አባቶች የእምነት ምሳሌዎች የፅድቅ አርበኞች ቆራጥ ጨካኞች መንግሥታትን ድል ነሱ ጭፍሮችን አባረሩ ድልን ዘመሩ በድል ዘመሩ አዝ፦ በአምላኬ ሁሉ ይቻላል በጌታ ሁሉ ይቻላል (2x) ይቻላል አዎን ይቻላል ይቻላል በእርግጥ ይቻላል በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (2x) የእሳትን ሃይል አለፉ ክፉውን ጥሰው አለፉ በእምነት ድል ነሱ (2x) የአናብስትን አፍ ዘጉ በእምነት እያደጉ ሄዱ ተጠጉ (2x) አዝ፦ ይቻላል አዎን ይቻላል ይቻላል በእርግጥ ይቻላል በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (2x) ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል በጌታ ሁሉ ይቻላል (2x) ሃይልን በሚያስታጥቀን በአምላካችን ታምነን እንገባለን እንወጣለን ቃሉም እንደሚነግረን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን እንበልጣለን ችሎ የሚያስችለኝ ጌታ እያለኝ ለምን ስንፍናን አወራለሁኝ አዝ፦ ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል በጌታ ሁሉ ይቻላል (2x) እንወራረዳለን ለምስሉ አንሰግድም ጌታ ይረዳናል (2x) እውነትን እንሸሽግም በወንጌል ደግሞ አናፍርም ኢየሱስ ያድናል (2x) አዝ፦ ይቻላል አዎን ይቻላል ይቻላል በእርግጥ ይቻላል በእግዚአብሔር ዐይን እጅግ ቀላል ነው እኛ ያቃተን ለእርሱ ምኑ ነው (2x) ለአምላኬ ሁሉ ይቻላል በጌታ ሁሉ ይቻላል (4x)