አዝ፦ ዲያቢሎስ ምነው ቸኮለ ሊውጠን እየከጀለ መሰለኝ ቀኑ ሊደርስ የሰይጣን መንግስት ሊፈርስ በእርግጥ ቀኑ ደርሶ ነው የሚይዘው ግራ ገብቶት ነው (፫x) የገባው ደረቱን ነፍቶ ነጋሪት ከበሮ መቶ ሲወጣ በጣር ተይዞ በጌታ ኢየሱስ ስም ታዞ ፡ አይተናል ዛሬም ይሆናል የኢየሱስ ስሙ ያድናል ሌባ ነው ነፍስን ይሰርቃል ከህይወት መንገድ ያርቃል አይገባም በዋናው በር ይያዛል መስኮት ሲሰብር ሲሸፍት እንደ ልማዱ ደቆሰው ኢየሱስ በክንዱ አድራሻው አመድ አተላ እንደ ከብት አሳር ሲያበላ የለውም ክብር ማእረግ አያውቅም ሰው ማሳደግ ኢየሱስ አዳነን ከእጁ ሆ በሉ ስሙን አውጁ ለመስቀል እንጨት ሲቆርጥ መዶሻ ሚስማር ሲሰጥ መቃብር ድንጋይ ሲገጥም ዘብ ሲያቆም ማእተም ሲያትም ፈርቶ ነው ይህ ሁሉ አበሳ አልቀረም ኢየሱስ ተነሳ