እምነት ሲለካ በሰፈር ጓዳ ሲፈተሽ በችግር (አሃሃ) ዐይኖች በእምባ ሲሞሉ ኃያል ጉልበቶች ሲላሉ (ኦሆሆ) የሠማይ የምድር ጌታ ሆይ ስንጠፋ አይገድህም ወይ (አሃሃ) ማለት አልቀረም ይሆናል ጌታ ግን ደርሶ አድኖናል (ኦሆሆ) ከእግሩ ስር ዝቅ ብለን ልናከብረው ይገባናል (አሃሃ) አዝ፦ የገባው ሲያመሰግን ያልገባው ሲያጉረመርም ስህተት ፈላጊዎች ሲያሙ እየተራወጡ ሲሻሙ (ኦሆሆ) መገለጥ ከላይ ሲለቀቅ ዲያቢሎስ በታች ሲጨነቅ (እህህ) ዳዊቶች ሲፈነጥዙ ሚልኮሎች ደግሞ ሲያፌዙ (ኦሆሆ) ሁሉም ስራውን ይሰራል ነበር አለ ይኖራል (አሃሃ) እኔም ስራዬን እሰራለው ለአምላኬ እዘምራለሁ (አሃሃ) በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃያል ስሙን አከብራለሁ (አሃሃ) የዓለም ሙገሳን ነቀፋን በመስማት ጊዜን አናጥፋ (አሃሃ) ተረት ጨዋታ ይቅርብን አስቸኳይ ስራ አለብን (አሃሃ) መመሪያው በእኛ ከሰራ አይደርስብንም ኪሳራ (አሃሃ) ነገር ሚስጥሩ ደርሶናል ካከበርነው ያከብረናል (አሃሃ) ምሥጋና ስንሰዋለት ማዳኑንም ያሳየናል (አሃሃ) አዝ፦ የገባው ሲያመሰግን ያልገባው ሲያጉረመርም ስህተት ፈላጊዎች ሲያሙ እየተራወጡ ሲሻሙ (ኦሆሆ) መገለጥ ከላይ ሲለቀቅ ዲያቢሎስ በታች ሲጨነቅ (እህህ) ዳዊቶች ሲፈነጥዙ ሚልኮሎች ደግሞ ሲያፌዙ (ኦሆሆ) ሁሉም ስራውን ይሰራል ነበር አለ ይኖራል (አሃሃ) እኔም ስራዬን እሰራለው ለአምላኬ እዘምራለሁ (አሃሃ) በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃያል ስሙን አከብራለሁ (አሃሃ) መንፈስ ዘወትር ዝግጁ ነው ሥጋም እንደሆነ ደካማ ነው አሃሃ ፊት ካሳዩት ካዘኑለት አይመቸው አይሞላለት ኤሄሄ እንዳይገፋን በትዕቢቱ መጐሸም ነው መድሃኒቱ አሃሃ ጉድለት ብቻ እየቆጠርን ማጉረምረሙን እንተውና (አሃሃ) ቀና እንበል ጌታን እንይ በምሥጋና ድል አለና (አሃሆ) አዝ፦ የገባው ሲያመሰግን ያልገባው ሲያጉረመርም ስህተት ፈላጊዎች ሲያሙ እየተራወጡ ሲሻሙ (ኦሆሆ) መገለጥ ከላይ ሲለቀቅ ዲያቢሎስ በታች ሲጨነቅ (እህህ) ዳዊቶች ሲፈነጥዙ ሚልኮሎች ደግሞ ሲያፌዙ (ኦሆሆ) ሁሉም ስራውን ይሰራል ነበር አለ ይኖራል (አሃሃ) እኔም ስራዬን እሰራለው ለአምላኬ እዘምራለሁ (አሃሃ) በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃያል ስሙን አከብራለሁ (አሃሃ) ሳይጀምረኝ ልከምረው ዛሬን ከሰጠኝ ልኑረው (አሃሃ) በማለዳ ልነሳና ድምጼን ላውጣ በምሥጋና (አሃሃ) ወፎች ለምን ይቅደሙኝ ላሰማቸው ሳያሰሙኝ (አሃሃ) ቀኑን ልቀድስ ለጌታ በዝማሬ አፌን ልፍታ (አሃሃ) የመምጫውን ቀን ማን ያውቃል ዛሬም ቢሆን ማራናታ አዝ፦ የገባው ሲያመሰግን ያልገባው ሲያጉረመርም ስህተት ፈላጊዎች ሲያሙ እየተራወጡ ሲሻሙ (ኦሆሆ) መገለጥ ከላይ ሲለቀቅ ዲያቢሎስ በታች ሲጨነቅ (እህህ) ዳዊቶች ሲፈነጥዙ ሚልኮሎች ደግሞ ሲያፌዙ (ኦሆሆ) ሁሉም ስራውን ይሰራል ነበር አለ ይኖራል (አሃሃ) እኔም ስራዬን እሰራለው ለአምላኬ እዘምራለሁ (አሃሃ) በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ኃያል ስሙን አከብራለሁ (አሃሃ)