ምድር ለሰው ልጆች ተሰጥታለች አልፋ (2x) ሁሉም በየሙያው ይላል ቀና ደፋ (2x) ከዚህ ወዲያ አይባል ከዚያ በመለስ (2x) ቅዱሱ ይቀደስ እርኩሱም ይርከስ (2x) አይቶ ሰምቶ የለየ ነጸነት አለው እንስበከው እንጂ ጡንቻ አናሳየው ያሻውን ይከተል ሰው እንደገባው ሰይፋችን ይመለስ ወደ ሰገባው አዝ፦ ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ (ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ) ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን) ምድር ተባርካለች በሃይማኖት ብዛት (2x) ህመሟ ባሰ እንጂ አንዱም አልፈወሳት (2x) ምድር ተባርካለች በሃይማኖት ሃብት (2x) እንትንና እንትን እንትን በሚሉት (2x) አሁንም ይፈልቃል በየቀበሌው እናትና አባት አያት የሌለው አንዱ ካላዳነ አያድንም ሺሁ ወገኔ ተመለስ ይቅርብህ እልሁ አዝ፦ ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ (ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ) ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን) በስራ ይገለጥ የያዝነው እምነት (2x) ሙታንም ይነሱ ይውጡ አጋንንት (2x) ዳንኩኝ ተፈወስኩኝ ብለው ይመስክሩ (2x) የሃይማኖት ፋይዳ ይህ ነው ቁም ነገሩ (2x) የሚያድን እምነት የሚያደርስ ሠማይ ከሌለው ሰው አልፎ ሰርቶ አይበላም ወይ በሰላም እንደር አይረበሽ ሰፈር ድንበር አትለፉ ተዉ አንደፋፈር አዝ፦ ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ (ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ) ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን) ደርሶ ስም ለማጥፋት ወሬ አሉባልታ (2x) ጭራሽ ይባስ ብሎ በአስክሬን ጨዋት (2x) ትዳርን አፋቶ ልጅ ከእናት ነጥሎ (2x) ከቀ. (1) . ከሰፈር ከማህበር አግልሎ (2x) ከገነት ሊገባ እንዲያው መታሰቡ ቁርጥህን እወቀው አትደርስ ከአጠገቡ አሳደህ እሰረው ግደልልኝ ያለ ዲያቢሎስ ነው እንጂ እግዚአብሔር አይደለ አዝ፦ ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ (ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ) ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን) የእኔ ይበልጣል ቢሉ ምንም ክፋት የለው (2x) እኛ ማንስማማው ዛቻ ሲጀመር ነው (2x) እግዚአብሔር ትልቅ ነው ለሁሉም ይበቃል (2x) ምስክር ነው እንጂ አያሻው ጠበቃ (2x) እናንት የአምላክ ልጆች ከቶ አትታወኩ ሁሉም በየቋንቋው ይጩህ ወደአምላኩ የሁሉም ማንነት በተግባር ይታያል የኤልያስ አምላክ በእሳት ይለያል አዝ፦ ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ (ሰምቶ የሚመልስ በእኛ ላይ ይንገሥ) ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን (ወርዶ የሚያድን እርሱ አምላክ ይሁን)